Friday, October 05, 2018

የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ

(መስከረም 25፣ 2011 (አዲስ አበባ)))--የመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት(ዩኒቨርስቲ ) ምደባ ዛሬ ከ8 ሰዓት ጅምሮ ይፋ መሆኑን የሃገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ።

ምደባው የተማሪዎችን ውጤት፣ የፊልድ እና የዩንቨርስቲ ምርጫ፣ የዩንቨርስቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የወንዶችና የሴቶችን ምጥጥን ማዕከል ባደረገ እንዲሁም የልዩ ድጋፍ ተጠቃሚዎችን /በማጥባት ላይ የሚገኙ ሴቶችን ያገናዘበ መሆኑን ተገልጿል።

እንዲሁም ዓይነ ስውራንን፣ መስማት የተሳናቸውን፣ አካል ጉዳተኞችን/ በተጨማሪም የጤና እክል ያለባቸው እና ከታወቀ የመንግስት ሆስፒታል የሜዲካል ቦርድ ማረጋገጫ ያቀረቡት ላይ የማጣራት ስራዎችን ካካሄደ በኋላ ምደባው መዘጋጀቱን አስታውቋል።፡፡

ተማሪዎች ወደ ተመደቡበት የትምህርት ተቋማት በሚሄዱበት ወቅት የነገዋ ኢትዮጵያ በትከሻቸው ላይ መሆኗን በመገንዘብ ለትምህርታችሁ ትኩረት እንዲሰጡ ኤጀንሲው አሳስቧል። ተማሪዎች ምደባችሁን በኤጀንሲው ድረ-ገጽ app.neaea.gov.et በመግባት ማየት እንደሚችሉ ነው የተነገረው።
ኤፍ.ቢ.ሲ

1 comment:

Post a Comment