Friday, February 01, 2013

ለወንዶች መዘነጫም መገልገያም

(Feb 01, 2013, አልማዝ አያሌው)--ዘናጮች፣ ተሽቀርቃሪዎች፣ ፋሽን ተከታዮች ሲባሉ የሚሰሙት ሴቶች ናቸው። ውበታቸውን ለመጠበቅ ሲሉ የፀጉር፣ የጫማ፣ የልብስ፣ የቦርሳ... ፋሽኖችን ይከተላሉ። ማች (አመሳስለው) ይለብሳሉ። 

ከሀገር ውስጥ አልፈውም የባህር ማዶ ፋሽን ይከተላሉ። ዛሬ ዛሬ ደግሞ ከሴቶች ባልተናነሰ መልኩ ፋሽን ተከታይ የሆኑ ወንዶች ቁጥር ከፍተኛውን ቦታ እየያዘ ነው ዲዛይነሮቻችንም ይህንኑ በማየት ሊሆን ይችላል የወንዶች ፋሽን የሚባሉትን ይዘው ብቅ እያሉ ነው። 
 

ይህ በፎቶግራፍ ላይ የምትመለከቱት ወጣት የያዘው የቆዳ ቦርሳ፣ ያደረገው ኮፍያ እና ስከርቭ ዲዛይን ያደረገችው ወይዘሮ ዓይናለም አየለ ናት። ዲዛይነሯ እንደምትለው ከሆነ የእዚህ ዓይነቱ ፋሽን ቦርሳ ወንዶች ለአይፖድ (ዘመናዊ መረጃ መያዣ) መያዣነት የሚጠቀሙበት ነው። «ቱሪስት ባግ» እየተባለም ይጠራል። 

ወደ መዝናኛ ሥፍራ ወጣ የሚል ወይም ደግሞ ወደ ሥራና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሲያመራ ለመዘነጫም፣ ለመገልገያም ሊጠቀምበት ይችላል። ኮፍያውም ከቦርሳው ጋር ማች ተደርጐ (ተመሳስሎ) ከቆዳ እና ከሸራ የተሠራ ነው። 

የወቅቱ አየር ቀዝቀዝ በሚልበት የማለዳው እና የምሽት ወቅት ከቦርሳውና ከኮፍያው ጋር ተመሳሳይነት ያለው የአንገት ስካርቭ ማድረግም እጅግ ዘመናዊ (ፋሽን) ተከታይ ያደርጋል። ይህንን የወንዶች ፋሽን ከወጣትነት ዕድሜ እስከ ጐልማሶቹ ድረስ ቢጠቀሙበት እጥፍ ጠቀሜታ እንዳለው ትመክራለች ዲዛይነሯ።
አዲስ ዘመን ጋዜጣ 

No comments:

Post a Comment