(Feb 12, 2013, አስመረት ብስራት, አዲስ አበባ)--ፀጉር ከጽንስ ጀምሮ አብሮ የሚፈጠር፣
የሚያድግ እና የሚሞት የሰውነታችን ክፍል ነው። የፀጉር ያለጊዜው መመለጥ፣ መሸበት፣ መነ ቃቀል፣ መሰባበርና መሳሳት
የብዙ ሰዎች ችግር ነው። ፀጉር ላይ የሚከሰቱ ችግሮችና መፍት ሔዎቻቸውን በተመለከተ በአለርት ሆስፒታል የቆዳና
የአባለዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ከሆኑት ዶክተር ሽመልስ ንጉሤ ጋር ቆይታ አድገናል።
ጤናማ የሆነ የፀጉር አበቃቀል ዑደት አለ
ስንል ፀጉር የዕድገት ጊዜውን ጠብቆ ያድጋል። በሂደትም ዕድገቱን በማቆም ይረግፋል ማለታ ችን ነው። ፀጉር ከሁለት
እስከ ሦስት ዓመት ያድጋል። ለሁለትና ለሦስት ወራት ማደጉን አቁሞ ደግሞ የሚረግፍበት ዑደት ጤናማ የፀጉር አበቃቀል
ዑደት እንለዋለን። ሁለት ዓይነት የፀጉር አበቃቀል ዑደት አለ። «ኦናጂ» እና «ቴሌጂን» ይባላል።
አብዛኛውን ጊዜ ፀጉር በፍጥነት ማደግ የሚችልበት ዑደት «ኦናጂ ን» ሲሆን በቀጣይነት ፀጉር ማደጉን የሚያቋርጥበትና የሚረፍግበት ጊዜ «ቴሌጂን» ይባላል። በራስ ቅላችን ላይ ወደ 100 ሚሊዮን የሚጠጉ የፀጉር ዘለላዎች በየሦስት ወሩ ይበቅላሉ። በአንፃሩ ደግሞ በየቀኑ ከ50 እስከ 100 የሚደርሱ የፀጉር ዘለላዎች ይረግፋሉ።
የፀጉር ችግሮች ምን ምን ናቸው?
የፀጉር ችግሮች ከምንላቸው ከፍተኛ የሆነ የፀጉር መርገፍ፣ ራሰ በራነት ፣ ያለዕድሜ በሽበት መወረር፣ በሴቶች ላይ የሚወጣ ፂም፣ የፀጉር መበጣጠስና መነቃቀል ተጠቃሽ ናቸው። በፀጉር ላይ ከሚታዩት ችግሮች በዋነኛነት
የሚጠቀሰው ራሰ በራነት በሁለቱም ፆታዎች ላይ ሊከሰት ይችላል። ልዩነቱ በሴቶች ላይ የፀጉር መሳሳት ሲያመጣ
በወንዶች ላይ ሙሉ ለሙሉ ፀጉርን የማንሳት ለውጦችን ያስከትላል።
ችግሩ ላይ የተደረጉ ጥናቶት እንደ
ሚያመለክቱት በሁለቱም ፆታዎች ከሦስት ሰዎች አንዱ የዚህ ችግር ሰለባ ነው፡፡ ከአሥራዎቹ እስከ ሠላሳዎቹ ባለው
ዕድሜ ውስጥ መከሰት የሚጀምረው ይህ ችግር የወንዶችን የራስን ቅል ፊት ለፊት ወይም የመሐል ክፍል ብቻ ለይቶ ፀጉር
አልባ ያደርጋል።
የችግሮቹ መንስኤዎቹ ምን ምን ናቸው? የራሰ
በራነት አንዱ መንስኤ በተፈጥሮ ከዘር የመወራረስ ሁኔታ ሲሆን በዋነኛነት በሆርሞን ውስጥ የሚገኘው ቴስቶስሮን
ችግር ሲያጋ ጥመው የፀጉር ዕድገትን ያስተጓጉላል። ይህ ሁኔታ የወንዶችን ፀጉር የሚመልጥ ሲሆን የሴቶችን ፀጉር
ያሳሳል።
ሴቶች ላይ ወሊድንና ማረጫ ጊዜን ተከትሎ
የሚመጣው የሆርሞን ለውጥና ከወለዱ እስከ ሦስት ወር ያለው ጊዜ ፀጉራቸው የሚጎዳበት ወቅት ነው። የልብ በሽታ፣
የደም ግፊትና ከባድ ትኩሳት በሚኖርበት ወቅት ፀጉር ይረግፋል። የተለያዩ መድኃኒቶችን መጠቀምም ለችግሩ መንስዔ
ሊሆን ይችላል።
በሌላም በኩል ከሥነ ልቦና ጋር በተያያዘ
ከፍተኛ ውጥረት እና ጭንቀት በሚያጋጥምበት ወቅት የፀጉር መነቃቀልና መሰባበር ሂደትን ያፋጥነዋል። ሰዎች በከባድ
ኀዘን ሲዋጡም ፀጉር ይረግፋል። ፀጉርን አብዝቶ ሹሩባ መሠራት፣ ከፍተኛ እሳት፣ ብዙ ማበጠር፣ የተለያዩ ቀለሞች
ሻምፖ እና ኮንዲሽነሮችን አብዝቶ መጠቀም የፀጉር መርገፍን ከሚፈጥሩ ነገሮች ውስጥ ይካተታሉ።
ታይሮይድ ሆርሞኖች ሲበዙና ሲቀንሱም ፀጉር
የመነቃቀልና የመሰባበር ሁኔታ ያጋጥመዋል። የደም ማነስ የሰውነት ውስጥ የብረት ማዕድን መጠን አነስተኛ መሆን፣
በምግባችን ሁኔታ ላይ ለምሳሌ የፕሮቲንና የአዮዲን እጥረት ሲኖር የፀጉር ዕድገት ይገታል። በሌላም በኩል በኢንፌክሽኖችና በፈንገስ የሚከሰቱ በሽታዎች ፀጉር ላይ ለሚደርሱ ጉዳቶች የራሳቸው ሚና አላቸው።
ያለ ዕድሜ መሸበት የሚፈጠረው ቀለም የሚያመርቱ ሚላኖሳይት የሚባሉት ሴሎች በሚጎዱበት ጊዜ ነው። በዚህ ወቅት ፀጉር ቀለም አልባ ይሆናል። ይህም ለሽበት መፈጠር ምክንያት ይሆናል።
መፍትሔዎቹ ምን ይሆኑ?
መጀመሪያ ፀጉሩ ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ
ምርመራ ማድረግ ይገባል። በዚህ መሠረት የመጠቀሚያ ቅባቶች ያደረሱት ጉዳት ካለ፤ ከሌሎች በሽታዎች ጋር የተያያዘ
እንደሆነና ከጭንቀት እና ከኀዘን ጋር የሚያገናኘው ነገር ካለ ምርመራ ይደረጋል። በተፈጥሮ በሽታን የመከላከል አቅም
ከፍተኛ መሆን ፀጉር አብቃይ ሴሎችን በማጥቃት ላሽ ያስከትላል። አንዳንድ ሴቶች ላይ በሚከሰት ኦቫሪያን ዲዝዝ
የሴቶች እንቁላል አምራች ክፍል በዕጢ ሲጎዳ ሆርሞን ይበዛል። የሆርሞኑ መብዛት የወንድነትን አካላዊ ባህሪ
ስለሚያዳብር በሴቶች ፊት ላይ ፀጉር (ፂም) ይበቅላል። እነዚህንና የመሳሰሉ ችግሮችን ለመለየት የአልትራሳውንድ ምርመራ ይደረጋል።
የደም፣ የአልትራሳውንድና የተለያዩ
ምርመራዎች በማድረግ የፀጉሩን ያለፈ ታሪክ በማየትና ውጫዊ ችግሮች ላይ በመመርኮዝ ሕክምና ይሰጣል። የፀጉር ችግር
የሆነው መመለጥ ሲያጋጥም መድኃኒት በክኒን፣ በመርፌ፣ በቅባትና በሻምፖ መልክ ይታዘዛል።
በፈንገስ ለሚከሰቱ ኢንፌክሽኖች አንቲፈንገስ ክኒንና ሻምፖዎች ይታዘዛሉ። በብዛት ለሚከሰተው የፀጉር መነቃቀልና የመሳሰሉት ችግሮችና ተያይዞ ለሚመጣው የፀጉር መመለጥ ሜኖክሲድን 5 ከመቶ የሚባል መድኃኒት ይታዘዛል።
የፀጉር ችግር በምርመራ ከታወቀ በኋላ
ተገቢውን ሕክምና ከመውሰድ ጎን ለጎን የተመጣጠኑ ምግቦችን መመገብ ጤናማ የፀጉር ዕድገት ዑደት እንዲኖር ይረዳል።
እንደ ፕሮቲን፣በፍራፍሬ የበለፀጉ ምግቦች፣ ዚንክና ማዕድናትን የያዙ ምግቦችን መመገብ በጣም ጠቃሚ ነው።
ቀለምና ሌሎች ኬሚካሎችን ፣ የአገ ልግሎት
መጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው የፀጉር ቅባቶችን አብዝቶ ሹሩባ መሥራት፣ የተለያዩ ፀጉር የሚጎዱ አሠራሮችን መጠቀም፣
ለፀጉር መሰባበር ስለሚዳርግ ከእነዚህ መቆጠብ ይገባል።
የፀጉር ችግሮች እንዳይገጥሙ ለማድረግ ባለሙያ ከማማከር አንስቶ ፀጉርን በንጽሕናና ወዙን በጠበቀ መልኩ በመንከባከብ ጤናማ ፀጉር ማግኘት ይቻላል። በተረፈ በሳይንሱ ብዙም ማረጋገጫ ባይ
ገኝላቸውም ከተለያዩ የተፈጥሮ ቅጠላ ቅጠሎች የሚዘጋጁ የፀጉር ቅባቶችን መጠቀም ለፀጉር ጤንነት ሊረዳ ይችላል።
በአጠቃላይ በፀጉር ዙሪያ ለሚከሰቱ ችግሮች ሕክምና ባለሙያ ጋር መነጋገሩ ውጤታማ የሚያደርግ ሲሆን ከችግሮቹ ጋር
ተያይዘው ለሚመጡ የሥነልቦና ጫናዎችም ባለሙያ ማማከር መፍትሔ ይሰጣል።
አዲስ ዘመን ጋዜጣ
No comments:
Post a Comment