(Oct 11, 2013, (አዲስ አበባ))--የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተሰላፊ ጌታነህ ከበደ ዋሊያዎቹ ከናይጀሪያ ጋር አዲስ አበባ ላይ በሚኖራቸው ወሳኝ የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ላይ ላይሰለፍ እንደሚ ችል እየተገለጸ ነው፡፡
ጌታነህ ከበደ ለደቡብ አፍሪካው ቢድቬስት ዊትስ እየተጫወተ ሲሆን፣ ቁርጭም ጭሚቱ ላይ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ለእሁዱ የአዲስ አበባ ጨዋታ እንደማይደርስ ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙሀን በዘገባቸው ጠቁመዋል፡፡ የ21 ዓመቱ ጌታነህ ኢትዮጵያ በዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ ውጤታማ እንድትሆን ካስቻ ሏት ወሳኝ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ከመሆኑም በላይ ግቦችን በማስቆጠር ውጤታማነቱን አስመስክሯል፡፡
ከዋሊያዎቹ ጋር ለመቀላ ቀል ከትናንት በስቲያ አዲስ አበባ የገባው ጌታነህ ቀደም ሲልም ኢትዮጵያ ከመካከ ለኛው አፍሪካ በነበራት ጨዋታ ላይ በጉዳት ምክንያት አልተሰለፈም ነበር፡፡ አሁን ደግሞ በድጋሚ ናይጀሪያን ከሚገጥመው የዋሊያዎቹ ስብስብ ውጪ መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
ይህን ተከትሎ አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ትኩረታቸውን ሙሉ ለሙሉ ኢትዮጵያ ባደረገቻቸው የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ዎች ላይ ተሰልፎ አራት ግቦችን ባስቆጠረው ሳላዲን ሰኢድ አህመድ ላይ አድርገዋል፡፡ ሳላዲን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከናይጀሪያ አቻው ጋር በ2011 አዲስ አበባ ላይ2ለ2 ሲለያይ ሁለቱንም ግቦች ሳላዲን ማስቆጠሩ ይታወሳል፡፡
ጌታነህ ከበደ ዋሊያዎቹ ባደረጓቸው የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ደቡብ አፍሪካ ላይ አንድ፣ ቦትስዋና ላይ ሁለት በአጠቃላይ ሦስት ግቦችን ማስቆጠሩ ይታወሳል፡፡
ከአዲስ ዘመን

No comments:
Post a Comment