(Sept 02, 2012, Addis Ababa)--የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አስከሬን ከንጋት 11 ሰዓት ጀምሮ በታላቁ ቤተ መንግስት የፀሎተ-ፍትሃት ስነ ስርዓት ተደርጎለት ለመጨረሻ ስንብት መስቀል አደባባይ ደርሷል፡፡
በታላቁ
ቤተ መንግስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት
አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ፣ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ አምባሳደሮች፣ የሃይማኖት
አባቶች፣ የመከላከያና የፖሊስ አባላት፣ ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ተገኝተዋል፡፡
የጠ/ሚኒስትሩን አስከሬን የያዘውን ሳጥን ሰረገላ ላይ ያሰቀመጡት በጀነራል ሳሞራ የኑስ የተመሩ የሀገር መከላከያ ጀነራል መኮንኖች ናቸው፡፡ አስከሬኑም በወታደራዊ ክብር ዘብና በማርሽ ባንድ ታጅቦ ነው ወደ መስቀል አደባባይ ያመራው፡፡ በመስቀል አደባባይም የተለያዩ አገራት መሪዎችና ተወካዮቻቸው፣ የመከላከያና ፌደራል ፖሊስ ሰራዊት፣ የመንግስት ሰራተኞችና እንግዶች አስከሬኑን ለመቀበል በስፍራው ተገኝተዋል፡፡
መስቀል አደባባይ
3ሰዓት ከ10 ደቂቃ ላይ በሞተረኞች የታጀበው የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ አስከሬን ከላይ ቀይ ከስር ጥቁር ባደረጉ የማርሽ ባንድ አባላት ዝግ ያለ ዜማ ታጅቦ መስቀል አደባባይ ደርሷል፡፡
በልብሰ ተክህኖ የደመቁ ካህናት አስክሬኑን ከፊትና ከኋላ አጅበውታል፤ ጥቁር የለበሱ የመከላከያ ዘብም በሁለቱም ጎኖች ተሰልፈው ነው ያጀቡት፤
መስቀል አደባባይ ሲደርሱ የቀድሞ ታጋዮች የትግል ልብሳቸውን ለብሰው በለቅሶና ዋይታ፤ አስከሬኑን ተቀብለዋል፤ በስፍራው የሚገኙ በርካታ ሰዎችም በእንባ እየተራጩ ነው አስከሬኑን የተቀበሉት፡፡
በመስቀል አደባባይ በአሁኑ ከ3 ሰዓት 15 ጀምሮ በኦርቶዶክስ የሃይማኖታዊ ስርዓት መሰረት ፀሎት እየተካሄደ ነው፤ 3 ሰዓት ከ25- የአዲስ አበባ ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ የስንብት ስነ ስር ዓቱን በህሊና ፀሎት አስጀምረዋል፤
በመቀጠልም የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ንግግር ያደረጉ ሲሆን «ኢህአዴግና መንግስት የህዝቡን እምባ ማበስ የሚቻለው በጠራ መስመራችንና የመሪያችንን ጽናት ተላብሰን በእልህና በቁጭት ጠንክረን ለመስራት ቃል በመግባት ነው።» ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአካል ቢለዩም ጠንካራው የትግል መንፈሳቸው ከእኛ ጋር ስለሆነ ከቀብር ስነ ስርዓቱ ማግስት ጀምሮ ኢህአዴግና መንግስት ውጤታማ ተግባር ለመፈፀም ከፍተኛ ርብርብ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
ጠቅላይ
ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም ህዳሴ የሰሩ፤ በተለይም የአፍሪካ ቀንድ እንዲረጋጋ ጠንካራ ስራ የሰሩ
ሲሆን ይህንንም ተግባራቸውን መንግስት አጠናከሮ እንደሚቀጥልም ነው አቶ ኃይለማርያም የተናገሩት። የአዲስ አበባ ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ የስንብት ስነ ስርቱን በህሊና ፀሎት አስጀምረዋል፤
በመቀጠልም የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ንግግር ያደረጉ ሲሆን «ኢህአዴግና መንግስት የህዝቡን እምባ ማበስ የሚቻለው በጠራ መስመራችንና የመሪያችንን ጽናት ተላብሰን በእልህና በቁጭት ጠንክረን ለመስራት ቃል በመግባት ነው።» ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአካል ቢለዩም ጠንካራው የትግል መንፈሳቸው ከእኛ ጋር ስለሆነ ከቀብር ስነ ስርዓቱ ማግስት ጀምሮ ኢህአዴግና መንግስት ውጤታማ ተግባር ለመፈፀም ከፍተኛ ርብርብ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
ጠቅላይ
ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም ህዳሴ የሰሩ፤ በተለይም የአፍሪካ ቀንድ እንዲረጋጋ ጠንካራ ስራ የሰሩ
ሲሆን ይህንንም ተግባራቸውን መንግስት አጠናከሮ እንደሚቀጥልም ነው አቶ ኃይለማርያም የተናገሩት። Read more from ERTA »
1 comment:
ye hagere hizb hoy Egzabher Yibarkh Yikedshm Ethiopia Kemelkam Amerar Gar Beselam Tinur
Post a Comment