Showing posts with label Opinion | Spotlight. Show all posts
Showing posts with label Opinion | Spotlight. Show all posts

Thursday, September 05, 2019

የኢትዮጵያን አንድነት ከሚፈረካክሱ ድርጊቶች መታቀብ ይገባል!

(Sep 05, (አዲስ አበባ))--እንዳለመታደል ሆኖ ነው እንጂ ኢትዮጵያ ታላቅ አገር ነበረች፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብም በዓለም የታሪክ መዝገብ ደማቅ አሻራ ያሳረፈ ነበረ፡፡ አሁንም ከታሰበበት ኢትዮጵያን ታላቅ ማድረግ አያቅትም፡፡ ኢትዮጵያዊነትንም የኅብረ ብሔራዊነት ማጌጫ ማድረግ አያዳግትም፡፡ ነገር ግን ለማይረቡና ለማይጠቅሙ ጉዳዮች ከመጠን በላይ ትኩረት እየተሰጠ፣ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በማራከስ የተፈጸመው ነውረኛ ድርጊት ሥሩን እያስረዘመ ነው፡፡

Monday, August 19, 2019

ከመፍትሔ ይልቅ ችግር መቆለል የማይወጡት አዘቅት ውስጥ ይከታል!

(Aug 19,(ሪፖርተር))--ነገሮችን በማወሳሰብ ችግር ለመፍጠር ግንባር ቀደም የሆኑ፣ ከሰላም ይልቅ ግጭት የሚቀናቸው፣ ስህተት ለማረም ሳይሆን ስህተት ፍለጋ ላይ የተጠመዱና በአጠቃላይ አገርን ቀውስጥ ውስጥ ለመክተት የሚባዝኑ በዓይነትም በቁጥርም እየጨመሩ ነው፡፡ ከአቅሟ በላይ ችግሮች የተቆለሉባት ኢትዮጵያን ከድጡ ወደ ማጡ እየገፉ ያሉ ኃይሎች አንድም ቀን ተሳስተው ለሰላም፣ ለጋራ ዕድገትና ለአብሮነት ሲማስኑ አይታዩም፡፡ በየዕለቱ የፀጥታ ሥጋትና የሕዝብ መከራ ሆነው ያሳቅቃሉ፡፡

Sunday, August 11, 2019

ፖለቲከኞች ከመጠማመድ ወደ መደማመጥ ተሸጋገሩ!

(Aug 11, (ሪፖርተር))--ከ40 ዓመታት በፊት ኢሕአፓና መኢሶን በመስመር ልዩነት ምክንያት ደም አፋሳሽ ጠላትነት ውስጥ ሲገቡ፣ የቃላት አጠቃቀማቸው ጭምር አንዱን ከሌላው መለያ እንደነበር ብዙ ተብሎበታል፡፡ እነዚህ የማርክሲዝም ርዕዮተ ዓለም ይከተሉ የነበሩ ድርጅቶች ንፋስ ሊያስገባ በማይችል ልዩነት ጠላትነት ከመፍጠራቸውም በላይ፣ ለአንድ ትውልድ ጦስ የሆነ መከራ እንዲደርስ ምክንያት ሆነዋል፡፡

ማፈርስ በራሳችን ነው!

(Aug 11, (ሪፖርተር))--የኢትዮጵያ ስታዲየሞች በሙሉ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽንን (ካፍ) ዝቅተኛውን መሥፈርት ስለማያሟሉ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚከናወኑ ዓለም አቀፍ ግጥሚያዎች ወደ ጎረቤት አገር እንደሚሄዱ ሰሞኑን ተሰምቷል፡፡

Friday, August 09, 2019

ማፈርስ በራሳችን ነው!

(Auu 09, (ሪፖርተር))--የኢትዮጵያ ስታዲየሞች በሙሉ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽንን (ካፍ) ዝቅተኛውን መሥፈርት ስለማያሟሉ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚከናወኑ ዓለም አቀፍ ግጥሚያዎች ወደ ጎረቤት አገር እንደሚሄዱ ሰሞኑን ተሰምቷል፡፡ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በፊት የካፍ መሥራች አባል የነበረችው ኢትዮጵያ፣ ዝቅተኛውን መሥፈርት ማሟላት ባለመቻሏ ስታዲየሞቿ ከዓለም አቀፍ ውድድር ሲታገዱ መስማት ትልቅ ኃፍረት ነው፡፡ ይህ አንገት የሚያስደፋ ኃፍረት ብዙዎችን የሚያሳዝንና የሚያበሳጭ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ነገር ግን ቆም ብሎ ዙሪያ ገባውን በማየት ዘርፈ ብዙ አገራዊ ጉዳዮችን መመርመር ያስፈልጋል፡፡

Sunday, June 30, 2019

አብን አመራሩን ጨምሮ ከ350 በላይ አባላቱና ደጋፊዎቹ መታሰራቸውን አስታወቀ

(30 Jun, (ክሪፖርተር))--የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ (አብን) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባሉን ጨምሮ፣ ከ350 በላይ አባሎቹና ደጋፊዎቹ መታሰራቸውንና እየታሰሩም መሆኑን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ይከበር!

(30, Jun (ሪፖርተር ))--ታሪክ እንደሚመሰክረው ጨዋነት፣ አስተዋይነት፣ ታጋሽነት፣ አዛኝነት፣ ጀግንነት፣ አገር ወዳድነት፣ ወዘተ. የኢትዮጵያ ሕዝብ መገለጫ ናቸው፡፡ ይህ ታሪካዊ ሕዝብ ሌብነትን፣ አስመሳይነትንና ሸፍጠኝነትን ይፀየፋል፡፡ አጉል ጀብደኝነትና ከንቱ ፉከራም አይጥመውም፡፡ ታላላቆችን ማክበርና ለታናናሾች አርዓያ መሆን ዘመናትን የተሻገረ ባህል ነው፡፡ ሕዝባችን ችግሮች ሲያጋጥሙት የሚፈታው በአስደማሚዎቹ የምክክር ባህሎቹ ሲሆን፣ በግለሰቦችም ሆነ በማኅበረሰቦች ውስጥ ፀብ ሲያጋጥም አስደናቂ የሆነ የዕርቅና የሽምግልና ሥርዓቶች አሉት፡፡


Saturday, January 12, 2019

የአገር ጉዳይ የልጆች ጨዋታ አይደለም!

(Jan 12, (ሪፖርተር))--በዚህ ዘመን ምራቃቸውን የዋጡ ሰዎች የወጣቶች መካሪ፣ የአገር ሽማግሌ፣ የትውልድ አርዓያና የተጣመመውን የሚያቀና መሆን ሲገባቸው፣ እንደ ሠፈር ጎረምሳ የብጥብጥና የሁከት ምንጭ ሲሆኑ ያሳዝናል፡፡ በፖለቲካው መስክ ከ40 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠሩ ፖለቲከኞችና የሚመሩዋቸው ድርጅቶች አድረው ቃሪያ ሲሆኑ ያሳፍራል፡፡ ለዓመታት በመሣሪያ ያልተሳካላቸውንና በሰላማዊ ጥሪ ያገኙትን መልካም አጋጣሚ የሚያበላሹ ያሳቅቃሉ፡፡ በኢትዮጵያ ምድር የተለያዩ አመለካከቶችና አጀንዳዎች ያሉዋቸው የፖለቲካ ኃይሎች በነፃነት የሚፎካከሩበትን ምኅዳር ለማመቻቸት በጋራ እንረባረብ ሲባል፣ በተሳሳተ መንገድ ለመንጎድ የሚሞክሩ ወገኖች ቆም ብለው ቢያስቡ ይበጃል፡፡

Saturday, September 29, 2018

አዳመጠች አረገዘችን አይሆንም

አንዳንድ ታሪክ ሲቆይ ተረት ይመስላል፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን እንድ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ድንቅ መምህር ነበሩ፡፡ ለተማሪዎቹ የሚሰጧቸው ቋሚ ትዕዛዛት ነበሩ፡፡ ተማሪዎቹም ያከብሩዋቸውና ይወዷቸው ስለነበር ለጥ ሰጥ ብለው ትዕዛዛቱን ይቀበሉና ይተገብሩ ነበር፡፡

ከጅብ ጅማት የተሠራ ክራር ቅኝቱ ልብላው ልብላው ነው!

ከዕለታት አንድ ቀን ጅቦች በጠፍ ጨረቃ ተርበው የሚበላ ፍለጋ ሲዘዋወሩ አንድ ግዙፍ ዝሆን ገደል ገብቶ ሞቶ አዩ፡፡
አንደኛው ጅብ - በረሀብ ከምንሞት እንግባና እንብላው
ሁለተኛው ጅብ - ገደሉ በጣም ሩቅ ነው፡፡ እንኳን ገብተን ሆዳችን ሞልቶ እንዲሁም ለመውጣት አዳጋች ነው፡፡

Tuesday, July 31, 2018

የደመርነውን መቀነስ ለምን?

(July 31, (አጀንዳ, የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ))--ሐምሌ 7 እና 8 ቀን 2010 ዓ.ም ለኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝቦች ልዩ ቀን ሆኖ በታሪክ ማህደር ሰፍሮ ይታወሳል። ሁለቱ አገራት ከሃያ ዓመታት በላይ የዘለቀውን መቃቃር የጥላቻን ግንብ አፍርሰው በመካከላቸው የነበረውን ጥቁር መጋረጃ ቀደው አዲስ የታሪክ ምዕራፍ በፍቅር ከፍተዋል። በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና በኤርትራው ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ፊት አውራሪነት ምናልባትም ከወር በፊት የታሰብ የማይመስል የሚመስለውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት በፍቅርና ይቅር ባይነት ነብስ ዘርተውበታል። ይህም በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ጭምር የተወደሰና ለዓለም በምሳሌነት የሚጠቀስ ሠናይ ተግባር መሆኑን ታላላቅ መገናኛ ብዙሃን ሲያራግቡት ከርመዋል።

Saturday, July 14, 2018

የቀን ጅቦች የትም አሉ

(July 07(አጀንዳ ))--በየዕለቱ በፍጥነት የሚለዋወጠው የፖለቲካችን ሁኔታ በመሰረታዊ ለውጦች እየታጀበ ይገኛል፡፡ ለመጣው ለውጥና ለተገኘው አንጻራዊ ሰላም እንዲሁም ለተፈጠረውም ሀገራዊ መግባባት የኢሕአዴግ ጥልቅ ተሀድሶ የድርሻውን አበርክቷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድም የመሪነት ሚናውን በብቃት በመወጣት ከጎረቤት አገራት ጋር ሰላም ለመፍጠር ከሚያደርጉት ጥረት ባሻገር፤ ለጉብኝት ሲሄዱ በተለያየ ምክንያት ታስረው የነበሩ ኢትዮጵያዊያን እንዲፈቱ ማድረጋቸው ለዜጎች የተሰጠውን ክብር ያመላከተ ነው፡፡

Saturday, June 02, 2018

ይቅርታና ፍቅር ያሸንፋል!!

(June 02, (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት))--ሀገራችን በአዲስ መንፈስ፣ ትጋትና ብሔራዊ መነቃቃት ወደፊት መጓዝ ቀጥላለች፡፡ ጥንታዊ ስልጣኔዋ በዘመናት ሂደት ቢያሽቆለቁልም ትልቅ ሕልም ያለን ሕዝብና ሀገር እንደመሆናችን ዛሬ ዳግም በታላቅ ትንሳኤ በእድገትና ልማት ወደፊት መራመድ ጀምረናል፡፡ የኢትዮጵያን ጥንታዊና ቀደምት የስልጣኔ አውራነት ዘመናት ያስቆጠሩ ስለመሆናቸው በተለያዩ ሀገራት ቤተመዘክሮችና ሙዚየሞች ተሰድረው የሚገኙ ድርሳናት ያረጋግጣሉ፡፡ አዎን ትልቅ ነበርን፡፡ ወደፊትም ታላቅና ኃያል ገናና ሀገር እንሆናለን፡፡

Saturday, July 25, 2015

አገሬ ሆይ !«የዓለም መሪዎች ሁሉ ገና ፊታቸውን ወዳንቺ ያዞራሉ»

(25,  Jul 2015, ((አዲስ አበባ))--ባለፉት ሳምንታት ሲነገሩ ከነበሩ ትኩስ መረጃዎች መካከል አንደኛው ጆሮን የሚስብና አጃኢብ የሚያሰኝ ነበር፤ «የልዕለ ኃያሏ አገር ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው» የሚለው መረጃ። ከዚያማ ከግራና ከቀኝ እየተሰጡ ስለነበሩት አስተያየቶች ትችቶችና ሙገሳዎች ማድመጥ የዕለት ተዕለት ሥራ ሆነ። የኋይት ሐውስ የፕሬስ ጉዳዮች ኃላፊ ጆሽ ኧርነስት የኦባማን ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ባበሰሩባት ምሽት «የኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት አሜሪካ ከአፍሪካ አገሮች ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከርና በአፍሪካ ኢንቨስት የማድረግ ቁርጠኝነት ያላት መሆኑን ለማሳየት ያለመ ነው» ሲሉ ተደመጡ።

Monday, March 23, 2015

Analysis: Egypt Forced to Negotiate on Nile Dam

(Mar 23, 2015, (Business Insider Australia))--Egyptian President Abdel Fattah al-Sisi will travel to Addis Ababa on March 23 to address Ethiopian lawmakers before travelling to Sudan to sign an agreement on the Grand Ethiopian Renaissance Dam. The details of the agreement are unknown, but its aim is to balance Ethiopia’s economic interests with Egypt’s national security concerns.

Wednesday, March 04, 2015

በዓድዋ ጦርነት ለነጻነታችን ያሳየነው ወኔና ተጋድሎ ዛሬም በድህነት ትግሉ ሊደገም ይገባል

(Mar 04 (አዲስ አበባ))--ወራሪውን የኢጣሊያ ፋሽስት ስለረታንበት ታላቁ የዓድዋ ድል፤ ነጻነታችንን እንደጠበቅን ስለ መቆየታችን፤ ስለቀደሙት ጀግኖች አባቶቻችንና አያቶቻችን ማንነት፤ ለአገራቸው ሉዓላዊነትና ለሕዝባቸው ነጻነት ያደረጉትን አኩሪ ተጋድሎ፤ ስለጥንካሬያቸው፤ በዓለም ላይ ገኖ ስለሚነገረው ግዙፍና ገናና ታሪካቸው፤ ለአገራቸው ሲሉ ስላፈሰሱት ደምና ስለ ከሰከሱት አጥንት ለመዘከር፤ የድላቸውንና የህልፈታቸውን ታሪካዊ የመታሰቢያ በዓል ለአዲሱ ትውልድ ለመንገርና ለማስተማር ሲባል እነሆ በየዓመቱ የካቲት 23ን አገራችን ብሄራዊ በዓል አድርጋ ማክበር ከጀመረች ብዙ ዓመታት ተቆጥረዋል።

Monday, February 16, 2015

«አንድ ቋንቋ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ ሕዝብ የሚሉ ሁሉ ህወሓትን ይጠሉታል» -አቶ ስብሃት ነጋ ነባር ታጋይና የኢትዮጵያ የሰላምና የልማት ዓለም አቀፍ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር

(የካቲት 09/2007 , (አዲስ አበባ))--የመምህርነት ሙያቸውን ትተው ነበር በ1967 .ም ወደ ትግል የተቀላቀሉት። ከህወሓት ነባር ታጋዮች መካከል አንዱ ናቸው፤ አቦይ ስብሃት ነጋ። ህወሓት የተመሠረተበትን 40ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ዝግጅት ክፍላችን በህወሓት አመሠራረት፣ ዓላማና የትግል አግባብ ዙሪያ ከአቦይ ስብሃት ነጋ ጋር ያደረግነውን ቃለ- ምልልስ የመጀመሪያ ክፍል ይዘን ቀርበናል።

Wednesday, February 04, 2015

የማንነት ጥያቄ በ «ኦሮማይ» መጽሐፍ

(ጥር 26/2007, (አዲስ አበባ))--ዓመቱን ጠብቆ እንደሚመጣ በዓል በኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ ስሙ በየጊዜው ይነሳል። የብዙዎች መነጋገሪያ የሆነ ደራሲም ነው። እርሱ በመጽሐፉ ምክንያት በሞት ቢለይም ዛሬ ድረስ ስሙ ይዘከራል - ደራሲና ጋዜጠኛ በዓሉ ግርማ።