Thursday, March 30, 2017

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለአራት ወራት ተራዘመ

(መጋቢት 21፣ 2009, (የአዲስ አበባ))--የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለአራት ወራት እንዲራዘም ወስኗል።

ምክር ቤቱ ባካሄደው 21ኛ መደበኛ ስበሰባ ላይ የተገኙት የኮማንድ ፖስት ሰክሬተሪያትና የመከላከያ ሚንስትር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ አዋጁ እንዲራዘም የተፈለገው ባለፉት ስድስት ወራት የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም እና መረጋጋት ወደ ማይቀለበስበት ደረጃ ለማድረስ፣ በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮችን ለመቆጣጠር እንዲሁም ህብረተሰቡ አዋጁ አንዲቀጥል ያለውን ፍላጎት ከግምት በማስገባት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባላትም የአስቸኳይ አዋጁ እንዲራዘም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ አስተያየትና ጥያቄዎችን ካቀረቡ በኃላ ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ምክር ቤቱ ሰላምና ጸጥታን ለማስጠበቅ የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ ማራዘሚያ አዋጅ ከመረመረ በኋላ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡ በዚህ መሰረትም አዋጁ ለቀጣይ አራት ወራት ተራዝሟል፡፡
ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን



No comments:

Post a Comment