Sunday, October 09, 2016

አስቸኳይ ጊዜ አዋጅን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ...

(መስከረም 29፣ 2009, (ebc))--የሀገሪቱን ሰላም የማይሹ ኃይሎች  ከውጭ  ጠላቶች  ጋር  በማበር በሀገሪቱ ህዝብ  ሰላም፣ ፀጥታና ደህንነት  ላይ የደቀኑትን  ከፍተኛ  ስጋት ለመቀልበስ  የሚኒስትሮች  ምክር ቤት  ከትንናንት  ጀምሮ  የሚተገበር  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ  አዋጀ።




የሚኒስትሮች  ምክር ቤት በሀገሪቱ  እየደረሰ  ባለው የህይወት  መጥፋትና  ከፍተኛ   የንብረት  መውደም  ላይ  በሰፊው ከመከረ  በኃላ የአስኳይ ጊዜ አዋጅ  ማወጁን  የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር  ኃይለማርያም ደሳለኝ  ለኢትዮጵያ  ህዝብ  ባስተላለፉት መልዕክት ገልፀዋል።

በተለያዩ የሀገሪቱ  አካባቢዎች በተፈጠሩ ሁከቶች  የሰው ህይወት  ጠፍቷል፤ዜጎች በላባቸው ያፈሯቸውን  ንብረቶችና   የህዝቡ የራሱ  ሀብት የፈሰሰባቸው  መሰረተ  ልማቶች መውደማቸውንም በመግለጫቸው  አውስተዋል።

የሀገሪቱን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ  ብጥብጦችና ግርግሮች እየተፈጠሩ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ ይህን ሁኔታ  በመቀልበስ የህዝቡንና  የሀገሪቱን ብሄራዊ  ጥቅም  እንዲሁም አጠቃላይ  ህገ  መንግስታዊ  ስርዓቱን  ለማስጠበቅ ህግ መንግስቱን መሰረት በማድረግ  ምክር ቤቱ  ከትናንት ጀምሮ  የአስኳይ ጊዜ አዋጁን ማወጁን ተናግረዋል።

በነዚህ ኃይሎች ከሰሞኑ  የተፈፀሙ ድርጊቶች  በሌሎች ሀገራት እንደታየው ሁሉ የሀገሪቱን  ህልውና  አደጋ  ላይ የጣለ  መሆኑንም ተናግረዋል።     የአስኳይ ጊዜ አዋጁ በህገ  መንግስቱ የተደነገጉ መሰረታዊ  የሰብአዊ መብቶችንና  በቬና ኮንቬንሽን ጥበቃ  የሚደረግላቸው የድፕሎማቲክ  መብቶች   እንደማይጣሱም ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አስታውቀዋል። 

አላማውም ህዝብና  መንግስት  የጀመራቸውን  የመፍትሄ  ጥረቶች  ማፋጠን  መሆኑንም ነው የተናገሩት። የአስኳይ ጊዜ አዋጁ እንደሁኔታው እየታየ ለ6 ወራት ያህል የሚዘልቅ መሆኑም ተመልክቷል።

ዝርዝር መረጃዎችን  በሚመለከት መንግስት በተከታታይ ለህዝብ መረጃ  እንደሚሰጥምጠቅላይ ሚንስትር  ኃይለማርያም አመልክተዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በህገ  መንግስቱ የተደነገጉ መሰረታዊ ሰብአዊ መብቶችን እንደማጨምርና የቬና ኮንቬንሽን ጥበቃ እንዲደረግላቸው የሚደነግገው የድፕሎማቲክ መብቶችን እንደማይጥስ ጠቅላይ ሚንስትሩ ተናግረዋል። 

No comments:

Post a Comment