(ጥቅምት 05፣ 2009, (አዲስ አበባ))--ኮማንድ ፖስቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማስፈፀሚያ መመሪያ ዝርዝር ይፋ አደረገ። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ትናንት ጥቅምት 4፣ 2009 ባካሄደው ስብሰባ ኮማንድ ፖስቱ አዋጁን ለማስፈፀም የሚያስችለውን መመሪያ እንዲያዘጋጅ የሚያመላክት ደንብ ማፀደቁን ተልከትሎ ነው የአዋጁ ማስፈፀሚያ መመሪያ ዛሬ ይፋ የሆነው ።
ኮማንድ ፖስቱ ዛሬ ይፋ ያደረገው መመሪያ በተለያዩ አካባቢዎች የሚወሰዱ እርምጃዎችን በዝርዝር ለይቶ ለህዝቡ ይፋ ማድረግ አለበት ለሚለው የደንቡ አካል መልስ የሚሰጥ ነው ።የህዝብን ደህንነት እና ህገ መንግስታዊ ስርዓትን አደጋ በሚጥሉ የሁከት እና ነውጥ ተግባራት ተሳትፈው የተገኙ ግለሰቦች ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎችንም መመሪያው አካቷል።
31 አንቀፅ ባሉት በዚሁ መመሪያ መሰረት ፣ሁከትና ብጥብጥ እንዲሁም በህዝቦች መካከል መቃቃሮችን የሚፈጥሩ ይፋዊም ሆነ ድብቅ ቅስቀሳዎች በማናቸውም መልኩና ዘዴ ተልክለዋል። ከሽብተኛ ድርጅቶች ጋር የሚኖር መስተጋብርና በልሳኖቻቸውን መገልገል ላይም በተለይ እንደ ኢሳት፣ ኦ.ኤም.ኤን. እና መሰል የአሸባሪ ድርጅቶች ሚዲያዎች ላይ መመሪያው እገዳ ጥሏል።
ያልተፈቀደ ሰልፍና የአደባባይ ስብሰባ፣ ለህዝብ አገልግሎት አለመስጠት፣ በትምህርትና በስፖርት ማዘውተሪያ አድማ ማድረግ በክልከላው ተካተዋል።
ኮማንድ ፖስቱ ባወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማስፈፀሚያ መመሪያ በህዝባዊ ባዕላት ላይ ሁከትና ብጥብጥ ሊፈጥሩ የሚችሉ ቅስቀሳዎችን ማድረግና ማወክ ፣በመሰረት ልማቶች ላይ ጉዳት ማድረስ፣ሰላማዊ የትራፊክ እንቅስቃሴን ማወክ፣የህግ አስከባሪዎችን ስራ ማወክምን መመሪያው በፅኑ ይከለክላል።
ያልተፈቀደ አልባሳት መልበስ፣የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት፣ ህገ መንግስታዊ ስርዓትና የሀገር ሉዓለዊነትን የሚጎዳ ተግባር መፈፀም፣ያልተፈቀደ ቦታ መገኘት መምሪያው ካቀፋቸው ክልክላዎች ውስጥ ተካተዋል።
መቀመጫቸውን በኢዲስ አበባ ያደረጉ የውጭ አገራት ድፕሎማቶች ያለ ኮማንድ ፖስቱ እውቅና ውጭ ከአዲስ አባባ ከ40 ኪሎ ሜትር ራዲየስ ውጭ መንቀሳቀስ እንደማይችሉም ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል። የህግ አስከባሪ አካላት ትጥቃቸውን ለሶስተኛ ወገን አሳልፈው መስጠትና ያለ አስገዳጅ ምክንያት ከስራ መልቀቅና ፈቃድ መጠየቅ እንደማይችሉም ተቀምጧል።
ኮማንድ ፖስቱ በተወሰኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየለየ ይፋ የሚያደርጋቸውን ክልክል ተግባራት ለይቶ አስቀምጧል። እነዚህም የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ፣በልማት አውታሮችና በመሰረተ ልማቶች አቅራቢያ ከቀኑ 12 ሰዓት በኃላ እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ድረስ ከተፈቀደለት ሰራተኛ በስተቀር መንቀሳቀስ የህግ አስከባሪዎች አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ያስላቸዋል ይላል መመሪያው።
የሰዓት እላፊ በሚጣልበት ቦታና ጊዜ ክልከላን በመተላለፍ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ እንደማይቻልም ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል። በተጨማሪም መመሪያው መረጃ የመስጠት የመተባበር ግዴታንም አስተቀምጧል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማስፈፀሚያ መመሪያ የደነገጋቸውን ክልክላዎች ተላልፎ በተገኘ ግለሰብ ላይ ይወሰዳሉ ያላቸውንም እርምጃዎች ይዘረዝራል።
እርምጃዎቹም ካለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከሚደረግ ብርበራ አንስቶ በቁጥጥር ስርማዋልና የህግ አስከባሪዎች አስፈላጊውን አግባብነት ያላቸውን እርምጃዎች መውስድ የሚያችላቸውን ስልጣንንም ዘርዝሯል። ኮማንድ ፖስቱ ተጠርጣሪዎችን ለፍርድ ቤት በማቅረብና በተሃድሶ የሚለቀቁትን እየለየ የእርምት እርምጃ በመውሰድ አዋጁ ፀንቶ እስከሚቆይበት ጊዜና ሰላምና መርጋጋት እስኪ መለስ ድረስ አገሪቱን በበላይነት እንደሚመራም በመግለጫው
ሰባት አባላት ያሉት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት በጠቅላይ ሚንስር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚመራ ሲሆን የሀገሪቱ መከላከያ ሚንስትርምሴክሬታርያትሆኖ እንደሚያገለግል ከዚህ ቀደም በተሰጡት መግለጫዎች መገለፁ ይታወሳል።
ምንጭ: ከኢብኮ

No comments:
Post a Comment