Sunday, January 11, 2015

ጣይቱ ሆቴል የደረሰው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ.

(ጥር 3/2007 (አዲስ አበባ))--በኢትዮጵያ የሆቴሎች ታሪክ የመጀመሪያውና የአገሪቱ ታላቅ ቅርስ የሆነው ጣይቱ ሆቴል የእሳት ቃጠሎ ደረሰበት። መነሻው ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት ዛሬ ረፋዱ ላይ የተነሳው የቃጠሎ አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር ውሏል።



Onlookers gather outside the Taitu Hotel following a fire at the historical landmark built in 1907, in the capital Addis Ababa, Ethiopia Sunday, Jan. 11, 2015. A fire department official says the fire has damaged the hotel which featured the city's famous jazz club "Jazz Amba", now destroyed, which was frequented by foreigners and locals alike. (AP Photo/Elias Asmare)
The Itegue Taitu Hotel in Addis Ababa, was built in the early 1900s and became famous as the setting for British author Evelyn Waugh's 1938 satirical novel "Scoop" ©Zacharias Abubeker (AFP)
A man works amongst the wreckage after a fire ripped through the Itegue Taitu Hotel in Addis Ababa, on January 12, 2015 ©Zacharias Abubeker (AFP)
በአደጋው አብዛኛው የሆቴሉ ክፍል ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል። ቃጠሎው ከረፋዱ ሦስት ሰዓት አካባቢ ከታችኛው የህንፃው ክፍል የተነሳ ሲሆን እስከ ረፋዱ አምስት ሰዓት ድረስ በመቆየቱ የሆቴሉ ሙሉ ህንፃና በአቅራቢያው የሚገኙ የባንክና ሌሎች አገልግሎት መስጫ ቢሮዎች ላይ ጉዳት አስከትሏል።

የሆቴሉ  አስጎብኚ የሆኑት አቶ ተሾመ አየለ እንዳሉት ሆቴሉ የተሰራበት ቁሳቁሶች ያረጁ መሆናቸው ከረጅም የህንፃው ዕድሜ ጋር ተዳምሮ ቃጠሎው በአጭር ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ሥር እንዳይውል አድርጎታል።

በዚህም የጃዝ አምባ አዳራሽ፣ የሆቴሉ የምግብ አዳራሾችና የመኝታ ክፍሎች ሙሉ በሙሉ በቃጠሎው መውደማቸውን ነው የተናገሩት።

በህንፃው ላይ አገልግሎት ከሚሰጡ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የኅብረት ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ታዬ ዲበኩሉ በበኩላቸው የሀዋላና ሌሎች የባንክ አገልግሎት መስጫ ቢሮዎችን ጨምሮ የባንኩ ህንፃ በቃጠሎው መጎዳቱን ገልጸዋል።

በአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ጋሻው ፅጌ በበኩላቸው የእሳት አደጋውን መንስኤና የወደመው ንብረት ግምትን በማጣራት ላይ መሆናቸውን ገልጸው ምርመራው እንደተጠናቀቀ ሪፖርቱ ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ብለዋል።

በቃጠሎው ንብረት ከመጎዳቱ በስተቀር በሰው ላይ የከፋ ጉዳት አለመኖሩን የተናገሩት ኮማንደሩ ቃጠሎውን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የአካባቢው ማኅበረሰብ ላደረገው ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሆቴል የሆነው ጣይቱ በ1898 ነበር የሆቴል አገልግሎቱን መስጠት የጀመረው።
ምንጭ:  ኢዜአ

No comments:

Post a Comment