Friday, January 18, 2013

ባለሥልጣኑ ቦይንግ 787-8 አውሮፕላኖች በረራ ለጊዜው እንዲቆም አደረገ

(Jan 17, 2013, Addis Ababa)--ከባትሪ፣ ከፍሬን፣ ከነዳጅ ፍሳሽ (ማንጠባጠብ) እና አንዳንድ የቴክኒክ ችግሮች ጋር በተያያዘ የአቪየሽን ባለሥልጣኖች ድሪም ላይነር 787 ለጊዜው አገልግሎት መስጠት እንዲያቆም ወስነዋል፤



የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ቦይንግ 787-8 ድሪም ላይነር አውሮፕላኖች የበረራ አገልግሎት ለጊዜ እንዲቆም መደረጉን አስታወቀ፡፡ ዘመናዊ አውሮፕላኖቹ እንዲቆሙ የተደረገበት ዋና ምክንያት የእነዚህ ስሪት አውሮፕላኖች በሚበሩባቸው ሌሎች አገሮች በታየው የቴክኒክ ብልሽት ምክንያት ነው፡፡ 

በመሆኑም በአምራች ኩባንያው ተጣርቶ በአ ሜሪካን ፌዴራል አቪዬ ሽን አስተዳደር ይሁንታ እስኪያገኝና የአሠራር እርማት እስኪበጅለት ድረስ ባለሥልጣኑ ዓለም አቀፉ አሠራር መከተል ስላለበት ከብሔራዊ አየር መንገዱ ጋር በመተማመን ለጊዜው የአውሮፕላኖቹ በረራ እንዲቆም አድርጓል፡፡

በባለሥልጣኑ የአይሮፕላን ምዝገባና የበረራ ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክተር አቶ የኔ ሻውልን ጠቅሶ በላከው መግለጫ፤ ይህም እንዲሆን የተደረገው ለመንገደኞች ደህንነትና የአገሪቱን በረራ ደህንነት ደረጃ ለማስጠበቅ ሲባል ነው፡፡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለቤትነት በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ተመዝግበው የሚገኙ አራት የድሪም ላይነር አውሮፕላኖች አሉ፡፡

በእነዚህም አውሮፕላኖች ምንም ዓይነት የአደጋ መንስዔ ያልተከሰተ ቢሆንም ቀጣይ ምርመራ ተደርጎ ደህንነታቸው የበለጠ አስተማማኝ እስከሚሆን ድረስ አውሮፕላኖቹ አገልግሎት እንዳይሰጡ ተደርገዋል፡፡
Source: Ethiopian News Agency
 Home

No comments:

Post a Comment