Thursday, April 26, 2012

በለንደን ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ በማራቶን እነማንን ታሰልፍ ይሆን?

(ማክስኞ, 24 ሚያዝያ 2012 )--በመጪው የለንደን ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ በማራቶን እነማንን ታሰልፍ ይሆን የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል፡፡

ኢትዮጵያን በማራቶን የሚወክሉትን ሶስት አትሌቶች የመለየቱን ሂደት አጓጊ ያደረገው የማራቶን ፈጣን ሰዓት ያስመዘገቡ አትሌቶች በርካታ መሆናቸው ነው፡፡

በፈረንጆቹ 2012 በአለም ላይ ከተመዘገቡት 20 የማራቶን ውድድር ፈጣን ሰዓቶች ውስጥ 13ቱን ያስመዘገቡት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ናቸው፡፡ ባለፈው ጥር ወር ላይ አትሌት አየለ አብሽሮ በዱባይ ማራቶን የዘንድሮውን የአለም ፈጣን ሰዓት አስመዘግቧል ፤2፡04፡23 ፡፡ ዲኖ ስፍር 2፡04፡50 በማስመዘገብ አየለን ተከትሎ ገብቷል፡፡

የ2011 የሎስ አንጀለስ ማራቶን ሻምፒዮኑ ማርቆስ ገነቲ 2፡04፡54 ታደሰ ቶላ ደግሞ 2፡05፡10 ፈጣን ሰዓቶች አስመዘግበዋል፡፡

በሁለት ውድድሮች ብቻ ኢትዮጵያ ከስምንት የአለማችን ፈጣን ሰዓቶች ውስጥ ስድስቱን አስመዘግባለች፡፡ የቀድሞው የአለም የማራቶን ሪከርድ ባለቤት ኃይሌ ገ/ስላሴ በለንደኑ ኦሎምፒክ እንደማይሳተፍ ገልጿል፡፡ 18 ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከኃይሌ የተሻለ ሰዓት አስመዝግበዋል፡፡

የ2010 የኒውዮርክ ማራቶን ሻምፒዮኑ ገብረእግዚአብሄር ገብረማርያም እና በ2009 ጃፓን ላይ 2፡05፡18 በመግባት የራሱን ፈጣን ሰዓት ያስመዘገበው ፀጋዬ ከበደም በምርጫው ከግምት ውስጥ የሚገቡ ናቸው፡፡

አትሌቶቹ የምርጫው መስፈርት ሰዓት ሊሆን ይችላል የሚል ግምት ቢኖራቸውም ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በኩል ምንም የተባለ ነገር የለም፡፡ ጥያቄው ግን አሁንም የብዙዎች ነው፡፡ 
Source: ERTA

No comments:

Post a Comment