Thursday, December 16, 2010

መንግሥቱ ወርቁ አረፈ

Thursday, 16 December 2010 16:26 
በኩሩና ኮከቡ የኢትዮጵያና የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋችና አሰልጣኝ የነበረው መንግሥቱ ወርቁ በ70 ዓመቱ አረፈ፡፡ ቀብሩ ዓርብ፣ ታኅሣሥ 8 ቀን 2003 ዓ.ም.፣ በ 10፡00 ሰዓት፣ በቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን እንደሚፈጸም የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር የሕዝብ ግንኙነት  አስታውቋል፡፡
በ3ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ግብፅን 4 ለ2 አሸንፋ ዋንጫ እንድታገኝ  ሁለቱን ግቦች ያስቆጠረው መንግሥቱ ወርቁ በ3ኛው አፍሪካ ዋንጫ 3 ግብ በማስቆጠሩም የኮከብ ግብ አግቢነት ክብር አግኝቷል፡፡

መንግሥቱ ወርቁ በስድስት የአፍሪካ ዋንጫዎች የፍጻሜ ግጥሚያዎች የተሳተፈ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ የተገኘችበትን የ1974ቱ የሊቢያው 13ኛ አፍሪካ ዋንጫ ብሔራዊ ቡድኑን በአሰልጣኝነቱ ለውድድር ያበቃው መንግሥቱ ወርቁ እንደነበረ አይዘነጋም፡፡

No comments:

Post a Comment