Saturday, January 03, 2015

ሙስሊሙ ኅብረተሰብ በዓሉን ሲያከብር እስላማዊ አስተምህሮ ተግባራዊ በማደርገ ሊሆን ይገባል

(ታህሳስ 25/2007, አዲስ አበባ))--ሙስሊሙ ኅብረተሰብ የነብዩ መሐመድ የልደት በዓል ሲያከብር እስላማዊ አስተምህሮ የሆኑትን ሠላምን፣ አብሮነትና በመረዳዳት መንፈስ ሊሆን እንደሚገባው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳሰበ።


የነብዩ መሐመድ 1 ሺህ 489ኛ የልደት በዓል ዛሬ የእምነቱ ተከታዮች፣ ኡለማዎች፣ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በተገኙበት  በታላቁ አንዋር መስጊድ በድምቀት ተከብሯል። የምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ሼክ ከድር ማህሙድ እንደገለጹት ''ዕለቱ የነብዩን ታሪክና ለሰው ልጆች የነበራቸውን እዝነትና መልካምነት በማውሳት የሚከበር ቀን ነው'' ብለዋል።

ኅብረተሰቡ የኃይማኖቱና የአገሩን ሠላም ለማስጠበቅና ወደተሻለ የዕድገት ደረጃ ለማድረስ በጋራ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል። የአዲሰ አበባ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ዶክተር አህመድ አብዱራህማን በበኩላቸው ሙስሊሙ ኅብረተሰብ  እስልምናን

ሽፋን በማድረግ የሚደረጉ ጽንፍ የወጡ እንቅስቃሴዎችን እንደሚያወግዝ ገልጸዋል። እነዚህ ጽንፍ የወጡ አካሄዶች ለሙስሊሙ ኅብረተሰብ አንዳች ነገር እንደማይፈይዱ በመረዳት ሕዝበ ሙስሊሙ እምነቱንና አገሩን በንቃት እንዲጠብቅ አባታዊ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዓሉ የነቢዩ መሐመድ የሕይወት ታሪክና መልካም ተሞክሮ በመንዙማና በተለያዩ ዝግጅቶች ታጅቦ ተከብሯል።
ምንጭ:  ኢዜአ

No comments:

Post a Comment