Tuesday, April 16, 2013

ህንዳዊው የአማርኛ መማሪያ መጽሐፍ አስመረቀ

(Apr 16, 2013, (አዲሰ አበባ))--ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ ጥቂት ዓመታት አስቆ ጥሯል። ኢትዮጵያን ለመግለፅ ቃላት የሚያጥሩት ይህ ሰው ዶክተር ኬ ሼከር ይባላል። በመንገድ ላይ ያዩት ሁሉ ሰላምታ የሚሰጡት «ነመስቴ ባቡጂ» እያሉ  መሆኑ ዘወትር ያስገርመዋል። ምክንያቱም የሚችሉትን አንድ ቃል በመጠቀም ለህንዳውያን ያላቸውን ክብርና ለመግባባት መፈለጋቸውን  የሚያሳዩበት ሌላ መንገድ አልነበረምና።

«አንድ ሰው መረዳት ብቻ በሚችለው ቋንቋ ካናገርከው ወደ ጭንቅላቱ በአገሩ ቋንቋ ካናገርከው ግን ወደ ልቡ ትደርሳለህ» የሚለውን የኔልሰን ማንዴላን አባባል አጥብቆ ይደግፋል። ቋንቋ ሰዎችን ከሰዎች ለማግባባትና መልካም የሚባል ግንኙነት ከመፍጠር አንፃር የሚጫወተው ሚና ለዶክተር ሼከር ከሁሉ በላይ ይገዝፍበታል።

ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ የሚነገረውን ቋንቋ ለማወቅ የሚረዳው መጽሐፍ «አማርኛን በእንግሊዝኛ» በሚል የተዘጋጀ አንድ መጽሐፍ ብቻ ነበር ያገኘው። ይሁን እንጂ የአማርኛ ቋንቋን ለማወቅ ካለው ልዩ ፍላጎት የተነሳ ብዙ ቀን አልፈጀበትም ነበር። በቀላሉ አማርኛ ማንበብ በኮምፒውተር ላይ መፃፍ በመቻሉ ተበረታትቶ መጽሐፍ ለማዘጋጀት ትልቅ ራዕይ ይዞ ተነሳ።

«ለአገሩ ባዳ ለሕዝቡ እንግዳ» ቢሆንም በጣም አስቸጋሪ ነገሮችን ለመድፈር ያለው ፍላጎት ከፍተኛ ነበር። ብዙ ህንዳውያን ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ የሀገሪቱን ቋንቋ ለመልመድ ሲቸገሩ ተመልክቷል። አሁን ግን ቋንቋውን ሊለማመዱበት የሚችሉበትን አጋዥ መጽሐፍ ከብዙ ልፋትና ጥረት በኋላ «ህንድኛ በአማርኛ-ኢትዮጵያውያን ከህንዳውያን ልብ ጋር ተነጋገሩ» እና «በአማርኛ ከኢትዮ ጵያውያን ጋር ተነጋገሩ» የሚሉ ሁለት መጽሐፎችን ባለፈው ቅዳሜ  በሻላ መናፈሻ ለማስመረቅ በቅቷል።

ብዙዎችን የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ለመተርጎም ቢፈልግም የገንዘብ እጥረት ያገደው ሼከር ለወደፊት ሌሎች ቋንቋዎችን ለመፃፍ ትልቅ ራዕይ እንዳለው ይናገራል።ነገሮች ከተመቻ ቹለትም የተለያዩ ቋንቋዎችን በመተርጎም ሕዝቦችን እርስ በርስም  ለማስተሳሰርና መግባባትን ለመፍጠር ትልቅ ሀሳብ አለው።

«ህንድኛ በአማርኛ» የሚለው መጽሐፍ  ህንዳውያንን ከኢትዮጵያውያን ወዳጆቻቸው ጋር ለመግባባት እንደሚያግዛቸው ትልቅ እምነት አሳድሯል። «አንባብያን  በራሳቸው ቋንቋ ብቻሳይወሰኑ የሌሎችን ቋንቋ ሳይንቁ ለማወቅ ቢጥሩ እርስ በርስ መግባባትና እውቀት መለዋወጥ እንደሚችሉ» ዶክተር ሼከር ይናገራል።

 ዶክተር ሼከር በአሁኑ ሰዓት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ ሲሆን ሁለቱን መጽሐፍ  ጨምሮ 14 የሚጠጉ መጽሐፍትን  አሳትሟል። ከእነዚህ መካከል ትግሪኛ በአማርኛ፣ ኦሮሚኛ፣  ሀዲይኛ እንዲሁም በኑዌርኛ ቋንቋዎች የተዘጋጁ ቋንቋን ለማወቅ የሚረዱ መጽሐፍትን አዘጋ ጅቷል።  ለመጽሐፍቱ እውን  መሆን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ኢትዮ ጵያውያን ጓደኞቹ በትርጉም ሥራ እንደረዱት በምርቃቱ ዕለት ተናግሯል።
 አዲስ ዘመን ጋዜጣ

Related topics: 
Amharic language courses to be offered in Chinese Universities 

No comments:

Post a Comment