Sunday, June 16, 2013

ኢትዮጵያ ደቡብ አፍሪካን 2 ለ 1 አሸነፈች

(June 16, 2013, (አዲስ አበባ))--የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደቡብ አፍሪካን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለመጨረሻ የማጣርያ ውድድር አለፈ፡፡ ለ2014 የዓለም ዋንጫ ውድድር ለማለፍ እየተካሄደ ያለው የማጣርያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ዛሬ ሰኔ 9 /2005 ዓ/ም ተጫውቶ 2 ለ 1 አሸነፈ፡፡



ደቡብ አፍሪካ በርናርድ ፓርከር በ 33 ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ መሪነትዋ አስቀድማ ብትይዝም በ43 ደቂቃ ጌታነህ ከበደ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አቻ ያደረገች ጎል አስቆሯል፡፡

የደቡብ አፍሪካ ተጫዋች ፓርከር በሁለተኛ ግማሽ ጨዋታ  በራሱ ባስቀጠራት ግብ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን  2 ለ 1  አሸንፎ ወጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከሴንትራል ሪፐብሊክ አፍሪካ አንድ ጨዋታ እየቀረው ለቀጠይ የመጨረሻ የደርሶመልስ ውድድር አልፏል፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ወደ ጥሎ ማለፍ ከሚያልፉ 10 የአፍሪካ ሀገራት አንዱ መሆን ችለዋል ፡፡ እንዲሁም ግብፅና ኮትዲባር ከየምድባቸው ለሶስተኛ ዙር የደርሶመልስ ጨዋታ አልፈዋል፡፡
ምንጭ፡ ኢሬቴድ

No comments:

Post a Comment