(ሚያዝያ 23 ቀን 2004 (አዲስ አበባ) -- በምዕራብ
አርሲ ዞን በአሳሳ ወረዳ በሃይማኖት ሽፋን አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች ግጭት በመፍጠር በሰው ሕይወትና ንብረት
ላይ ጉዳት መድረሱ በጥልቅ እንዳሳዘነው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ገለጸ፡፡
ጉባዔው ድርጊቱን በማስመልከት ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ጉባዔው አባል ቤተ እምነቶችን አቅፎ ስለ ሠላም ደፋ ቀና በሚልበት ሁኔታና ሁሉም ሃይማኖቶች ሃይማኖታዊ አስተምህሮታቸውን መሠረት በማድረግ አክራሪነትን በሚያወግዙበት ወቅት በሰው ሕይወት ላይ አስከፊ ሕልፈት መፈጠሩ በጥብቅ የሚወገዝ ነው፡፡
በጥቂት ግለሰቦችና አንጃዎች የተፈጠረው ደም መፋሰስ የትኛውንም የሃይማኖት ቤተሰብ የማይወክል መሆኑን ገልጾ ለጥቃቱ ሰለባዎች ቤተሰቦች በሙሉ መጽናናትን ተመኝቷል፡፡
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ስድስት ቤተ እምነቶች የሃይማኖት ልዩነቶቻቸውን ጠብቀው በጋራ አገራዊ ጉዳዮች በተለይም በአገር ደረጃ ሠላምና መረዳዳት እንዲኖር በጋራ ለመሥራት የተቋቋመ ተቋም እንደሆነ ገልጿል፡፡
ተቋሙ ከተቋቋመበት ዋና ዋና ዓላማዎች መካከል በአገሪቱ ለዘመናት የኖረው የሃይማኖት መከባበርና መቻቻል ተጠብቆ እንዲቀጥል ለማድረግና "አክራሪነትን" ማለትም በጋራ መተዳደሪያው መሠረት "ከእኔ ሌላ ሃይማኖት የለም" በሚል አስተሳሰብ የሌላውን መብትና መኖር የሚጋፋ አስተሳሰብ ለማውገዝ እንደሆነም አመልክቷል፡፡
የጋራ ጉባዔው በፌዴራል ደረጃ ከተመሰረተ በኋላ በዘጠኙ ብሔራዊ ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች መዋቅሩን በማስፋት ላይ ላይ የሚገኝ ሲሆን በተለይም በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ ወደ ዞንና ወረዳ የሰፋበት ሁኔታ ተፈጥሯል ብሏል፡፡
Source: ENA (Ethiopian News Agency)

No comments:
Post a Comment