Friday, April 19, 2013

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከግብጹ ዛማሊክ ጋር ለመጫወት ወደ ካይሮ አቀና

(Apr 19, 2013, (አዲስ አበባ))--በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ አየተሳተፈ ያለው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ወደ 8ቱ ክለቦች ለማለፍ የፊታችን ቅዳሜ ከግብጹ ዛማሊክ ቡድን ጋር ላለበት ጨዋታ ሚያዝያ 10/2005 ማምሻውን ወደ ካይሮ ተጉዟል፡፡



ቡድኑ በቻምፒዮንስ ሊግ ማጣሪያው የማሊውን ጆሊባን በአጠቃላይ 3 ለ1 በመርታት ነበር ለደርሶ መልስ ጨዋታ ያፈው፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በኢትዮጵያ የክለቦች የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ታሪክ አዲስ ውጤት ነው ያስመዘገበው፡፡

የግብጹ ዛማሊክ 5 ጊዜ የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን በማንሳት ጥንካሬውን ያስመሰከረ ሲሆን ቅዳሜ ከቅዱስ ጊዮረርጊስ ክለብ በሚያደርገው ጨዋታም ትልቅ ግምት ሰጥቶ እንደሚዘጋጅ አስታውቋል፡፡ ቡድኑ አጥቂው አዳነ ግርማን በጉዳት ይዞ አልተጓዘም፡፡
ከኢሬቴድ
 Home

No comments:

Post a Comment