(14th October 2011)--ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ዋሽንግተን ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ከጤና ባለሙያዎች ጋር ተወያዩ፡፡
ውይይቱ የአምስት ዓመቱን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ለማሳካትና የኢትዮጵያ መንግስት በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ረገድ የሰራቸው ስራዎች ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ነው፡፡
ውይይቱ የአምስት ዓመቱን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ለማሳካትና የኢትዮጵያ መንግስት በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ረገድ የሰራቸው ስራዎች ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ነው፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው በውይይቱ ላይ አቶ ሃይለማርያም የአምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ አበረታችና በአገሪቷ መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣትና የአገሪቷን እድገት ለሚፈታተኑ ችግሮች ምላሽ ሰጪ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ አያይዘውም የመንግስት ጥረት በመላ አገሪቷ የመሰረተ ልማትን ማስፋፋት መሆኑን ገልጸው በተለይም የአምስት ዓመቱን ዕቅድ ከማሳካት አንፃር ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከፍተኛ ትኩረት እንደተሰጠው አብራርተዋል፡፡
ሚኒስትሩ አክለውም ይህንን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የውጭ እርዳታ ሳይታከልበት በአገር ውስጥ የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶችና የህብረተሰብ ክፍሎች የ7 ቢሊዮን ብር የቦንድ ግዥ መከናወኑን ገልጸው ይህንን ትልቅ ፕሮጀክት ለማሳካት ዳያስፖራው መንግስት ላቀረበው ጥሪ መነሳሳት እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡
የህክምና ዶክተሮችና የጤና መኮንኖች በአገራቸው የጤና መስክ ተሳትፎ እንዲያደርጉም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ምንጭ: የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
No comments:
Post a Comment