Friday, May 13, 2011

ግብፅ በህዳሴው ግድብ ላይ ተቃውሞ እንደሌላት የሀገሪቱ ጠ/ሚ ኢሳም ሻሪፍ ገለፁ-->

ሪፖርተር ምስክር ተስፋዬ. May 13, 2011
የግብጽ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሳም ሻሪፍ ግብጽ ከኢትዮጵያ ጋር ስላላት ግንኙነት ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት የግብጽ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሳም ሻራፍ እንዳሉት የአባይን የውሃ አጠቃቀም በተመለከተ ግብጽ ከዚህ በኋላ የምትጫወተው ሚና አዎንታዊ ነው፡፡

ኢትዮጵያ በምትገነባው የህዳሴ ግድብ ላይ ግብብፅ ተቃውሞ እንደሌላት ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡

ከዚህ በፊት ኢትዮጵያ ለግድቡ እርዳታ እንዳታገኝ ግብጽ ያደረገችው እንቅስቃሴ ስህተት እንደነበረም ተናግረዋል፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር ሁሌም በትብብር እንደምትሰራ ገልፀዋል፡፡

የግብፁ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሣም ሻራፍ በኢትዮጵያ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ማንም ሀገር የማንንም የልማት እቅድ ማስቆም እንደማይችል ገልፀዋል፡፡
Ethiopian gov news

No comments:

Post a Comment