Friday, May 13, 2011

የግብጽ ጠ/ሚ ኢሳም ሻሪፍ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገቡ

ሪፖርተር ሳሙኤል ከበደ, May 12m 2011
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

የኢትዮ ግብጽ ግንኙነት እጅግ ተቀዛቅዞ ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሳም ሻሪፍ አሁን ግን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር የሚያስችል አዲስ ምእራፍ መከፈቱን ተናግረዋል፡፡

ግብጽ ከኢትዮጵያ ጋር ዘርፈ ብዙ ግንኙነት የመመስረት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላትም አረጋግጠዋል፡፡


«የጉብኝቱ ዋነኛ አላማ ለአዲስ ምእራፍ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር ለመወያየት ነው፡፡ ለአዲስ ሁሉን አቀፍ ልማት ትብብር ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ነው፡፡  

ስለ ውሃ ብቻ አይደለም በተቀናጀ የኢኮኖሚ እቅድ አብረን የምንሰራበት ሁኔታ እናመቻቻለን ማህበራዊ ባህላዊና መሰል ዘርፎችን ሁሉ ባቀፈ መልኩ አጠቃላይ ትብብር ማድረግ እንፈልጋለን፡፡»

ሁሉንም ሀገር የመልማት መብት እንዳለው የተናገሩት የግብጽ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሳም ሻራፍ ከኢትዮጵያ ጋር በአባይ አጠቃቀም ዙሪያ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ መስኮች ተባበረን እንሰራለን ብለዋል፡፡የኢትዮ ጵያ መልማት የግብፅ መልማት ነውትብብራችን በጋራ ጥቅም ላይ ያተኩራል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

«በሁለታችንም ሀገሮች ልማት እንዲኖር ነው የምንፈልግው አንዳችን ለአንዳችን አስፈላጊ ነን፡፡ ለዚህ ነው ከአሁን ሰአት ጀምሮ መፈላለግ ያለብን ሁሉም የመልማት መብት አለው በኢትዮ የሚኖረው ልማት ለግብፅ እጅግ ጠቃሚ ነው በግብፅ የሚኖረው ልማትም እንዲሁ ለኢትዮ ጠቃሚ ነው»

በኢትዮ ጵያ በኩል ያለው የትብብር ፍላጎትም እጅግ አወንታዊ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
«በኢትዮ በኩል ያለውን ስንመለከት ሁሉም መልእክቶች በጣም አወንታዊ ናቸው እኛም ለአዲስ የልማት ትብብር አዲስ ምእራፍ መክፈት ነው የምንፈልገው ፡፡  

የኢትዮ ምላሽ ደግሞ እጅግ አወንታዊ ሆኖ አግኝተንዋል፡፡ ምክንያቱም በፊት የነበረው ግኑኙነት በጣም ቀዝቅዞ ነበር፡፡ በሁለቱ ሀገራት መካከል በጣም መራራቅ ነበር አሁን ግን ይሄን አስስወገድነው አዲስ የልማት ትብብር መፍጠር አለብን እያልን ነው ያለነው፡፡  ከአሁን በሗላ ከሌላው የአፍሪካ ክፍል ጋር ትብብር መፍጠር አለብን፡፡»
ሪፖርተር ሳሙኤል ከበደ
Ethiopian gov news.

No comments:

Post a Comment