(July 31, (አጀንዳ, የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ))--ለትንንሽ እግራቸው መጫሚያ እንዲሁም ክፉ ደጉን ላላየው ገላቸው ባለቀለማትና ምቹ አልባሽን አይሹም፡፡ አሊያም ደግሞ ደረጃውን የጠበቀ ቤተ ሙከራ ያለውና በሁለንተናቸው ብቁ የሆኑ መምህራንን የያዘ ትምህርት ቤትም ለጊዜው አላስፈለጋቸውም፡፡ እነዚህ ሁሉ እናት አገራቸው እንዳደጉት አገራት ሁሉ በኢኮኖሚዋ ከፍተኛውን ስፍራ ስትቆናጠጥ የሚመጡ ናቸው፡፡ አሁን ግን አንገብጋቢው ጥያቄያቸው ንጹህ የመጠጥ ውሃና ያልተቀናጣ ትምህርት ቤት ውስጥ መማር ብቻ ነው፡፡
ለዚህም ነው የነገዎቹ እንቦቃቅላዎች እጣ ፈንታ ከወዲሁ ያሳሰባቸው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ‹‹በቀን ለማኪያቶ ከምታወጡት ወጪ አንዷን ዶላር በመቀነስ በገጠሪቱ የኢትዮጵያ አካባቢ በሚኖሩ ህጻናት ስም ብትልኩ እኛ ከእርሷ አንድም ላንነካ ቃል እገባለሁ›› ሲሉ በቅርቡ ለፓርላማ አባላት ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት የተደመጡት፡፡
ከዚህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ማስተዋል የሚቻለው በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ለእነዚህ ህጻናት ጥቂት ለጋስነታቸውን ብቻ ነው እንዲያሳዩ የሚጠበቀው ፡፡ የድሆችን ጩኸት ሰምተው እጅግ በጣም ጥቂቷን ነገር በመቸር ጆሯቸውን እንዲሰጡ ብቻ ነው ፍላጎታቸው፡፡ እርግጥ ነው ለጋስ በመሆን ከእንጀራቸው ማካፈል ቢሹ ምላሹ መልካም ስለመሆኑ ለማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ የድሃውን የማያቋርጥ የኑሮ ትግልን በጥቂት ልገሳ ድጋፍ በመስጠት ብቻ እፎይታ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡
መቼም ጠቅላይ ሚኒስትራችን ወደ መንበሩ በመምጣት ተጨባጭ ለውጦችን ማሳየትና ማስመዝገብ ከጀመሩ እነሆ ከመቶ ቀናት በላይ ሆኗቸዋል፡፡ አብዛኞቻችን እንደምንረዳው ከአንደበት የሚወጣ ቃል የሰውን ልጅ ልብ የመስበር ኃይል እንዳለው ሁሉ ለማነጽም ሆነ ለማጽናናት ተወዳዳሪ አይገኝለትም፡፡
ባሳለፍናቸው ሦስት ወራት ውስጥ ብቻ ከዶክተር አብይ አንደበት የሚደመጡ ንግግሮች ብዙዎችን ‹‹አጃኢብ›› ያስባለ ከመሆኑም በላይ ለማንም በምንም መረታት የማይፈልጉትንም ልብ ማሸነፍ የቻለ ስለመሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ በተለይ ‹‹መደመር›› የሚለው ቃል ብዙዎቹን ያስማማ ከመሆኑም በላይ ቃሉ ህይወት በመዝራቱም ህዝቦች መነጣጠልን የማይፈልጉ ስለመሆናቸው ፍንትው አድርጎ ያሳየ ነው ቢባል አንዳች ግነት የለበትም፡፡ አንደበተ ርዕቱእ ከሆኑት ከእኚህ መሪ የሚወጣው እያንዳንዱ ንግግር ከጥልቅ ጉድጓድ እንደሚቀዳ ውሃ የማያልቅ ሲሆን፣ አርኪነቱም የዚያኑ ያህል መሆኑ ብዙዎቹን ያስማማል ብዬ አምናለሁ፡፡
ለዚህም ነው በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አገር ቤት በተደመጠ ንግግራቸውና ከንግግራቸው ጀርባም በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ቀልባቸው የተሳበው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአገር ግንባታ በጥቂቶች ብቻ መወሰን የለበትም፤ የሁሉንም ቀናነትና ትብብር ይሻል ባሉ ማግስትም ‹‹እኛም ከጎንህ ነን፤ ተደምረናልም›› ሲሉ የተደመጡት፡፡
ዶክተር አብይ ፤ ‹‹በውጭ ያሉ ዳያስፖራዎች የአገሪቱን ማህበራዊ ችግር ለመፍታት የሚውል የውጭ ምንዛሪ ለመላክ ፈቃደኛ ከሆኑ የ‹‹ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ›› ይቋቋማል፤ ይህም ለአገሬ ልጆች የጤና ተቋማትና ትምህርት ቤት ግንባታ ይውላል እንጂ ከላዩ አንዳች አይቆነጠርለትም የሚል ሐሳብ ባቀረቡ ማግስት ማለት ይቻላል ተቋሙ ተመስርቷል፡፡ በዚህ በተመሰረተው ተቋም እያንዳንዱ ዳያስፖራ በነፍስ ወከፍ አንድ ዶላር ቢያስገባ የችግርን ተራራ ከሚንዱት በጎ ፈቃደኞች ተርታ ይሰለፋል፡፡
እርግጥ ነው ምንም እንኳ ገንዘብ ለአገራዊ እድገት ትልቅ ፋይዳ ቢኖረውም፤ ብቻውን ግን ከተፈለገው ጫፍ ላይ አያደርስም፤ ከጥሪቱ እነሆ ብሎ ሳይሰስት ማቋደስ የሚችል ዳያስፖራ ለእናት አገሩም ራሱን አምባሳደር አድርጎ መሾም እንደሚገባም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡ በየትኛውም የዓለም ጥግ ያሉ ኢትዮጵያውን ለአገራቸው መልካም ስምና ዝና በታማኝነትና በእኔነት ስሜትም እንዲሰሩም ጥሪ ማቅረባቸው እሙን ነው፡፡
ዶክተር አብይ በዳያስፖራው ላይ አንዳች እምነት ያሳደሩትን ያህል አብዛኛዎቹ ዳያስፖራዎችም በምላሻቸው ከዚህ ቀደም አድርገውት በማያውቁት አይነት ፍቅርና አንድነት ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር የድጋፍ ሰልፍ በማድረግም ሆነ በሌላ መልኩ ከጎናቸው መሆናቸውን ሲገልጹ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ በቅርቡም በተለይ በአሜሪካ በሚደረገው የኢትዮጵያውያን ህዝባዊ ጉባኤ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ለመወያየት አስቀድመው ዝግጅት እያደረጉ ስለመሆናቸው በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡
ይህ ውይይትም ሆነ አብሮነት ዋጋው ከፍ ያለ መሆኑ ጠቀሜታው ለአንድ ወገን ብቻ እንዳልሆነ ልብ ሊባል ይገባል፡፡ በተለያዩ አገራት ያሉ ኢትዮጵያውያኑም ሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ፍላጎታቸው ለየቅል ከመሆኑም በላይ ለአንድ አይነት ጉዳይ አተያያቸውም የዚያኑ ያህል የተራራቀ እንደሆነ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን ይህ ብሄራዊ መግባባትን ለመፍጠር ያስችላል ተብሎ የሚጠበቀውን ጉባኤ ለማሰናዳትና ለማሳካት በተለያየ ጽንፍ የቆሙ አካላት በአንድ አይነት ዝማሬ ለውጤታማነቱ ሲያቀነቅኑ እየተደመጡ ይገኛሉ፡፡ ሁሉም የበኩሉን ለመወጣትም ተፍ ተፍ ሲል መሰንበቱም ‹‹ቸር ወሬ ያሰማን›› የሚያስብል ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡
የጉባኤው መሪ ሐሳብ ‹‹የጥላቻና የልዩነት ግንብን አፍርሰን የፍቅርና የአንድነት ድልድይ እንገነባለን” የሚል ነው፡፡ ይህ በዋሽንግተን ዲሲ የሚካሄደው የኢትዮጵያውያን ጉባኤ የተሳካ እንዲሆን የብዙዎቻችን ፍላጎትም ነው፡፡ ምክንያት ቢባል ደግሞ ጥላቻ በምንም መመዘኛ ማንንም አይጠቅምም፤ ልዩነትም ቢሆን ራስን ለማመጻደቅና ከፍ ከፍ ለማድረግ ከሆነ ሳቅን ወደ ሃዘን የመቀየር ብርታት ያለው ነው፡፡ በአንጻሩ ደግሞ ፍቅር ያደምቃል፤ አንድነትም ያሞቃል፡፡ አልፎ ተርፎም ያስተሳስራል፡፡
ብዙዎች እንደሚያውቁት የዳያስፖራም ልብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ስለ አገሩ መቆርቆር እየጀመረ ነው፡፡ በእርግጥ ከዚህ ቀደም መንግሥት በተለያየ መንገድ የዳያስፖራውን ልብ ለማግኘት ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም ማለት ይቻላል፡፡ ‹‹የዳያስፖራ ሳምንት›› በሚል የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያከናውን ቆይቷል፤ የአገሩንም ልማት ተዘዋውሮ እንዲጎበኝም ተደርጓል፡፡ ኧረ እንዲያውም ቦታም በመስጠት ልማቱን እንዲቀላቀሉም ብዙ ጥሯል፡፡ ይሁንና መንግሥት ያሰበውን ያህል ማሳካት አልቻለም፡፡ ‹‹ምነው›› ቢባል ምላሹ ልብ አልተገኘምና ነው፡፡
ልብንማ ማሸነፍ ተችሎ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ላይ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከሦስት ሚሊየን በላይ ይሆናልና ቁጥሩ ቀላል የሚባልም አይደለም፡፡ የቁጥሩ መብዛትም ሳይሆን ወሳኙ የልብ ዝግጁነት ነው፡፡አሁን ታድያ ጊዜው ቀርቧል፤ በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያኑና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ መልካምን ለማድረግ ከራሳቸውም ጋር ቃለ መሃላ የፈጸሙ ይመስላል፡፡
ለዚህ ደግሞ ትልቅ ምክንያት አላቸው፤ የአገራቸው ጠቅላይ ሚኒስትር በአገር ቤት እያደረጉ ያሉት የሠላም ጥሪና የአንድነት መንፈስ ውስጣቸውን በመኮርኮሩና በማስገደዱም ጭምር ነው፡፡ እንዲያውም ይህ መደመርን የሚሰብክ መሪ እንኳ የኢትዮጵያውያኑን ልብ ቀርቶ ወንድም የሆነውን የኤርትራውያንን ህዝብና መሪ ልብም ማሸነፍ በመቻሉም ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሌላ አንዳች ቀጠሮ ደርበው ሳይዙ ከሰሞኑ ወደ ምድረ አሜሪካ ኢትዮጵያውያኑንና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑን ብቻ ለማወያየት እንደሚጓዙ ይጠበቃል፡፡ ታዲያ በስፍራው የሚገኙ ሁሉም ማለት በሚያስችል ሁኔታ በጉጉት ሊቀበሏቸው መሰናዳታቸውንም በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን እየገለጹ ነው፡፡
እንግዲያስ መደመር ማለት መረዳዳት፣ መተጋገዝ፣ መደማመጥ እንዲሁም መተሳሰብ እንደመሆኑም ዳያስፖራው ከዚህ በኋላ ቀድሞ የነበረውን አገር ወዳድነት በማደስ ወገኑን አገሩን እንደሚያግዝ ይጠበቃል፡፡ እነርሱ የሚልኳት ጥቂቷ ገንዘብ የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለማቃለል ፋይዳው ትልቅ ነው፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ እንዳሉትም ለውጡን በአንድ ዓመት ውስጥ ማየት እንችላለን፡፡
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

No comments:
Post a Comment