Tuesday, May 14, 2013

ፍርድ ቤቱ የእነ አቶ መላኩ ፈንታን በዋስ የእንለቀቅ ጥያቄ አልተቀበለም

(May 14, 2014, (አዲስ አበባ))--ዛሬ ግንቦት6 /2005 ከሰዓት በኋላ  የተሰየመው ችሎትም በቃል ክርክሩ ላይ ውሳኔ  የሰጠ ሲሆን በእስካሁ ቆይታ በእነ አቶ መላኩ ፈንታ የክስ መዝገብ ውስጥ አቃቢ ሀግ የጠየቀውን የ14 ቀናት ቀነ  ቀጠሮን የፈቀደ ሲሆን ዋስትናም ከልክሏል ።

በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በቁጥጥር ስር የዋሉ የኢትዮዽያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር እና ሌሎች 24 ሰዎች ትናንት ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ተጠርጣሪዎቹ  የጸረ ሙስና አዋጅ በሚደነግገው መሰረት የጊዜ ቀጠሮ ሊጠየቅባቸው ነበር ትናንት ግንቦት 5/2005 ፍርድ ቤት የቀረቡት።

ተጠርጣሪዎቹ የቀረቡበት የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት አቃቢ ህግ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ማሟላት አለብኝ በማለት ባቀረበው  የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ ላይ የቃል  ክርክር አካሂዷል። ችሎቱ ተጠርጣሪዎቹን በሶስት የክስ መዝገብ በመከፋፈል ፍርድ ቤቱ የተመለከተ ሲሆን፥ በእነ መላኩ  የክስ መዝገብ ውስጥ  ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች ተካተዋል።

አንደኛው  ተጠርጣሪ አቶ መላኩ ፈንታ ጠበቃ ደንበኛቸው በዋስ ለመለቀቅ ያስችሏቸዋል ያሏቸውን ማስረጃዎች ለፍርድ ቤቱ በቃል አቅርበዋል። ዛሬ ግንቦት6 /2005 ከሰዓት በኋላ የተሰየመው ችሎትም በቃል ክርክሩ ላይ ውሳኔ  የሰጠ ሲሆን፥ በእስካሁ ቆይታ በእነ አቶ መላኩ ፈንታ የክስ መዝገብ ውስጥ አቃቢ ሀግ የጠየቀውን የ14 ቀናት ቀነ  ቀጠሮን የፈቀደ ሲሆን ዋስትናም ከልክሏል ።

በተመሳሳይ በእነ አቶ ገብረዋህድ መዝገብ ዛሬ ግንቦት6/2005የተካተቱትን አንድ ተጠርጣሪ ጨምሮ ለ12 ተጠርጣሪዎች አቃቢ ሀግ የጠየቀውን የ14 ቀናት ቀነ ቀጠሮ ጥያቄን ፍርድ ቤቱ ተቀብሏል። ከትናንት ጀምሮ የሚታሰብ በተጠርጣሪዎቹ ላይ የሚካሄደው ምርመራ ተጠናቆ ለግንቦት 19 እንዲቀርቡ አዟል።

በእነ አቶ መሀመድ ኢሳ መዝገብ ውስጥ የሚገኙ ተጠርጣሪዎች ከጠበቆቻቸው ጋር እንዳልተገናኙ በመግለፃቸው ፍርድ ቤቱ ከጠበቆቻቸው ጋር ተገናኝተው ለፊታችን አርብ እንዲቀርቡ በማዘዝ በአቃቢ ህግ የ14 ቀናት ቀነ ቀጠሮ ጥያቄ ላይ በእለቱ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ይዟል ። Read more from .ERTA (ኢሬቴድ) » 

Related topics:
የፀረ ሙስና ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል   
አገራችን ሙሰኞችን የመሸከም አቅም የላትም
የአቶ ገብረዋህድ ባለቤት በቁጥጥር ስር ዋሉ 

Ethiopia Arrests Minister and "Corrupt Government Officials"   
Ethiopia arrests minister, 11 others over corruption
Ending corruption in Ethiopia

1 comment:

Anonymous said...

ENANTE BE KEFITEGNA BALE SILTAN BICHA ATAREKURU MEMENGEL YALEBET KE KEBELIE GEMIRO NEW ERE SINT ALE BEYE
1 KEBELIE WOREDA AKABI HEG DAGHA WOZETE BE GUBO MISERA
2 WOHA KIFIL MEBRAT HAYEL HULIE GIZIE TEBIKO AGELGILOT YEMIZEGA AGEGILOT LEMAGNET GIBO YEMITEYEK KELALUN TITO YEMIAKABID YAGER TELAT MEHONU TAWKO BALE SILTANATU TIMHERT BISETACHEW TIRU NEW

Post a Comment