Monday, May 20, 2013

በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት አቶ ዳዊት መኮንን በቁጥጥር ስር ዋሉ

(May 19, 2013, (አዲስ አበባ))--ሰሞኑን በሙስና ወንጀል ተጠርጥርጥረው ሲፈለጉ ከነበሩት ግለሰቦች መካከል በድለላ ስራ ላይ የተሰማሩት አቶ ዳዊት መኮንን በሻሸመኔ ከተማ በቁጥጥር ስር ዋሉ'

የፌደራል ፖሊስ ለኢትዮጱያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እንዳስታወቀው ግለሰቡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው እንደሚፈለጉ ሲያውቁ ሸሽተው ወደ ኬንያ ለመግባት ጥረት ላይ ነበሩ'

ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው የፌደራል ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተጠርጣሪው ሻሸመኔ ላይ በቁጥጥር ስር አውሎአቸዋል'

ተጠርጣሪው  በአዲስአበባ እና አዳማ በሚገኙ የግምሩክ  ጣቢያወች የድለላ ስራ ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመለክታል'
ምንጭ፡ ኢሬቴድ

2 comments:

Anonymous said...

I am so happy regarding the corruption movement
keep up and put-em where they belong good job GOD BLESS ETHIOPIA

Anonymous said...

I AM SO HAPPY TOO GOOD JOB THE CORRUPTION IS TO MUCH NEED TO CLEAN UP THE HOUSE

Post a Comment