Monday, May 20, 2013

የመለስ ዜናዊ የልደት ቀን በዋሽንግተን ተከበረ

(May 19, 2013, (አዲስ አበባ))--ታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ ህዳሴና ለአፍሪካ እድገት እንዲሁም ለአለም ያበረከቷቸው የዲፕሎማቲክ ጥረቶችና ታላላቅ አስተዋጽኦዎች በዋሽንግተን ቅዳሜ ግንቦት 10/2005 በተዘጋጀ ስነስርዓት ተዘክረዋል፡፡

በዋሽንግተንና አካባቢው የሚኖሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውን በኢትዮጵያ ኤምባሲ የታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ ልደት በማክበር ስራዎቻቸውን ዘክረዋል፡፡

በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ ታዋቂ ምሁር ዶ/ር ጥላሁን በየነ መለስ ዜናዊ ከልጅነት እስከ አዋቂነት እድሜያቸው የነበራቸውን ልዩ ብቃት፣ ችሎታና ተሰጥኦ እንዲሁም የውጤታማነት አቅም በማድነቅ የአእምሮ ብስለት የነበራቸው ታላቅ መሪ እንደነበሩ አስታውሰዋል፡፡ Read more from ERTA »

No comments:

Post a Comment