(June 28,2012, Reporter)--በጋምቤላ ክልል ለሻይ ቅጠል ልማት በወሰደው ሰፊ መሬት ምክንያት ከፍተኛ ውዝግብ አስነስቶ የነበረው የህንድ ኩባንያ ጣውላ ሲያመርት ተገኘ፡፡
የህንዱ ኩባንያ ቬርዳንታ ነርቨስት ያመረተው ጣውላና ሥራ አስኪያጁ ሰኔ 14 ቀን 2004 ዓ.ም. በመዠንገር ዞን ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡
የመዠንገር ዞን ዋና ኃላፊ አቶ ሙሴ ገጃት ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ለኩባንያው መሬቱ የተሰጠው ለሻይ ቅጠል ልማት ቢሆንም ከሻይ ቅጠል ልማት ይልቅ በጣውላ ምርት ላይ ተሰማርቷል፡፡ “ኩባንያው ጣውላ የማምረት ፈቃድ የለውም፡፡ በሕገወጥ ተግባር ላይ ተሰማርቶ ተገኝቷል፤” ሲሉ አቶ ሙሴ ኩባንያው በፈጸመው ድርጊት መበሳጨታቸውን ገልጸዋል፡፡
አቶ ሙሴ ቬርዳንታ ከዚህ ሕገወጥ የጣውላ ምርቱ በተጨማሪ ከአካባቢው ነዋሪዎች ላይ በሕገወጥ መንገድ ሁለት ሺሕ ሔክታር የሚጠጋ መሬት መግዛቱ ተደርሶበታል በማለት አክለው ገልጸዋል፡፡
ቬርዳንታ ነርቨስት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በጋምቤላ ክልል ውስጥ ከግብርና ሚኒስቴር 3,012 ሔክታር መሬት ለሻይ ቅጠል ልማት መረከቡ ይታወሳል፡፡
ለኩባንያው የተሰጠው መሬት በጋምቤላ ክልል መዠንገር ዞን ጉደር ወረዳ ጉማሬ ቀበሌ ውስጥ ነው፡፡ ጉደር ወረዳም ሆነ ጉማሬ ቀበሌ ከፍተኛ የደን ሽፋን ያላቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡ ለዚህ ኩባንያ መሬቱ በተሰጠበት ወቅት የአካባቢው ነዋሪዎች ተቋውሞ ያነሱ ሲሆን፣ ለፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ተቃውሞቸውን በደብዳቤ ገልጸዋል፡፡
የካቲት 2002 ዓ.ም. ለፕሬዚዳንቱ በጻፉት ደብዳቤ ጠብቀው ያቆዩት ደን ከመጥፋቱ በፊት ፕሬዚዳንቱ እንዲያስቆሙ ጠይቀዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ በጉዳዩ ጣልቃ ገብተው ዕርምት እንዲወሰድ ለግብርና ሚኒስቴር በጽሑፍ ማሳሰቢያ ቢሰጡም፣ በአካባቢው ደን የለም በሚል ሚኒስቴሩ በወቅቱ ዕርምጃ አልወሰደም በማለት ተቃውሞ ማቅረባቸው አይዘነጋም፡፡
ኩባንያው በወሰደው መሬት ላይ ለሚያለማው የሻይ ቅጠል ልማት ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ 89.5 ሚሊዮን ብር ብድር መውሰዱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ነገር ግን ከሁለት ዓመት በላይ ኩባንያው በወሰደው ቦታ ላይ የሚገኙ ዕድሜ ጠገብ ዛፎችን እየቆረጠ ጣውላ በማምረት ተግባር ላይ መሰማራቱ ተደርሶበታል፡፡
የዞኑ ፖሊስ ኩባንያው ያዘጋጀውን አንድ መኪና ጣውላ በቁጥጥር ሥር ቢያውለውም፣ ቀደም ሲል ኩታ ገጠም በሆነው የደቡብ ክልል በኩል በርካታ ጣውላ ማጓጓዙን የሚጠቁሙ መረጃዎች እየወጡ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡
Source: Reporter

No comments:
Post a Comment