(ሚያዝያ 21 ቀን 2004 (ጋምቤላ)--በጋምቤላ ክልል
ትናንት አመሻሹ ላይ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት በእርሻ ልማት ሥራ ላይ የተሰማሩ አምስት ሠራተኞች ህይወት ሲያልፍ
ሌሎች ስምንት ሠራተኞች ደግሞ መቁሰላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ።
ህይወታቸው ካለፈው ሰዎች መካከል አንዱ የፓኪስታን ዜጋ አራቱ ኢትዮጵያውን መሆናቸውን ያስታውቀው መግለጫው ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ ከደረሰባቸው መካከልም አራቱ ፓኪስታውያን አራቱ ኢትዮጵያውያን ናቸው ብሏል።
ጥቃቱ የተፈፀመው በክልሉ ሰፊ የእርሻ ልማት ስራ ከተሰማራው ከሳወዲ ስታር ቢዝነስ ዋና የእርሻ ጣቢያ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘውና የመስኖ ቁፋሮ ከሚከናወነበት ስፍራ ነው።
በወንጀሉ ተሳትፎ አድረገዋል ተብለው የተጠረጠሩ አስር ሰዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል። በዚህ ፀያፍና ዘግናኝ ድርጊት የተሳተፉ ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ ፖሊስ ምርመራውን በማጣራት ላይ ይገኛል ብሏል መግለጫው።
በአሁኑ ወቅት በክልሉ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር አለመኖሩና የአካባቢው ሰላምም ሙሉ በሙሉ የተረጋገጠ መሆኑን ያስታወቀው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መግለጫ በክልሉና ፌዴራል የፀጥታ ኃይሎች ቅንጅት የተቋቋመ የምርመራ ቡድን ምርመራውን አጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቋል።
የክልሉ ፖሊስ ወንጀለኞችን በሕግ ፊት ለማቅረብ የጀመረውን ጥረት በማገዝ በኩል ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቋል።
የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ለሟቾች ቤተሰቦች የተሰማውን ልባዊ ሃዘን በመግለፅ በጥቃቱ የመቁሰል አደጋ ለደረሰባቸው ሰራተኞችም ሙሉ ጤንነትን ተመኝቷል ሲል የዘገበው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ነው።
Source: ENA (Ethiopian News Agency)

No comments:
Post a Comment