Wednesday, June 07, 2017

የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የእስራኤል ጉብኝት

(ግንቦት30፤2009, (አዲስ አበባ)))-- ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ሁለቱ ሀገራት በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ግንኙነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግሩ ገለጹ፡፡ እስራኤልና ኢትዮጵያ የአለም የልማትና የደህንነት ስጋት የሆነውን ሽብርትኝነትን እንደሚታገሉ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ተናግረዋል፡፡

በእስራኤልና በአፍሪካ ሀገራት መካከል የነበረው ወዳጅነት ተመልሶ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ሚና የላቀ እንደሆነ ኔታኒያሁ ገልጸዋል፡፡ እስራኤል የምትታወቅበትን የግብርና እና ውሃ ቴክኖሎጂ፤ ጤናና ሌሎች መስኮችን ለኢትዮጵያ ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል፡፡ ሽብርተኝነት የጋራ ጠላት በመሆኑ ተባብረን መዋጋት አለብን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ፡፡

በናዚ ጭፍጨፋ ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ 6 ሚሊዮን ያህል ይሁዳዊያን በተዘጋጀው ሃውልት ጠቅላይ ሚኒትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የአበባ ጉንጉን አኑረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን


No comments:

Post a Comment