(መስከረም 16/2007, (አዲስ አበባ))--የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶና የግብጹ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ትስስር ዘላለማዊ መሆኑን የአሌክሳንድሪያ ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ማርቆስ መንበረ ፓትሪያርክ ተናገሩ።
የአሌክሳንድሪያ ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ማርቆስ መንበረ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ዳግማዊ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በመስቀል ደመራ በዓል ላይ እንዲገኙ በተደረገላቸው ግብዣ መሠረት ከትናንት ጀምሮ በጉብኝት ላይ ናቸው።
ፓትሪያርኩ በዛሬው ማለዳ ቦሌ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ከእምነቱ ተከታዮች ጋር የቅዳሴና የጸሎት ሥነ ሥርዓት አካሂደዋል። ከሥነ ሥርዓቱ በኋላ ፓትሪያርኩ እንዳሉት ሁለቱ ዐብያተ ቤተክርስቲያን ስለ አገራቱ ሰላምና ዕድገት በጋራ እንደሚጸልዩ ገልጸው ፣ትስስራቸው ዘላለማዊ እንደሆነ ተናግረዋል።
ፓትሪያርኩ በዛሬው ውሎአቸው የጠቅላይ ቤተክህነት ቤተ መጻህፍትንና ሙዚየምን፣ የአዲስ አበባን ሙዚያምን በመጎብኘትና የደመራ በዓል ሥነ ሥርዓትን ይከታተላሉ። በዐብያተ ቤተክርስቲያኑ መካከል ያለው ወዳጅነት ከ1ሺህ 500 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ታሪክ አለው።አቡነ ቴዎድሮስ ኢትዮጵያን የጎበኙ አምስተኛው የግብፅ ጳጳስ ሆነዋል።
በጥር 2007 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ ማትያስ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋር በመሆን በግብጽ ይፋዊ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል። የእህትማማቾቹ ዐብያተ ክርስቲያን ግንኙነት ረጅም እድሜ ያስቆጠረ ቢሆንም፣ በአገሮቻቸው መካከል ያለው የእርስ በርስ ግንኙነት ወጥ አለመሆኑ ግንኙነታቸውን ሞቅና ቀዝቀዝ እያለ እንዲጓዝ አድርጎታል።
አገሮቹ በተለይም ከፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ወደ ስልጣን መምጣት በኋላ የትብብር መስኮቻቸቸውን በማስፋት በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ወዳጅነት በማካሄዳቸው የህዝብ ለህዝብ ትሰስሩ፤የንግድና ኢንቨስትመንት ልውውጡና የፖለቲካ ስምምነቶች እያደጉ መጥተዋል።
ምንጭ: የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት

No comments:
Post a Comment