Wednesday, December 18, 2013

አፈ ቅቤ ልበ ጩቤ

(Dec 18, 2013, (አዲስ አበባ))--ከዚህ ቀደም «በጋዜጠኛ ግፊት የተሰጠ ማስተባበያ» በሚል ርዕሥ ባቀረብኩት ፅሁፍ የኢትዮ ጵያ ብሄራዊ የመረጃ ደሕንነትና የፌዴራል ፖሊስ የጋራ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል ኢትዮጵያ ላይ የሽብር ጥቃት የመፈፀም እቅድ መኖሩን አስመልክቶ ያወጣውን መግለጫ መነሻ በማድረግ በቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራም ወትዋችነት በአፍሪካ ሕብረት የኤርትራ አምባሳደር ግርማ አስመሮም የሰጡትን ማስተባበያ አንስቼ ነበር፡፡ በዚህ ፅሁፍ ደግሞ የቪኦኤው ጋዜጠኛ አምባሳደር ግርማ አስመሮምን በስልክ አቅርቦ ማስተባበያ እንዲሰጡ ያደረገበት ምክንያት ምን እንደሆነ ተጨባጭ መረጃዎችን በመጥቀስ ለማቀረብ ወድጃለሁ፡፡

የቪኦኤው ጋዜጠኛ ዋነኛ ዓላማ የኤርትራ መንግስት ለኢትዮጵያ ህዝብ ንፁህ መስሎ እንዲቀርብ ማድረግ ነው፡፡ ካለምንም የንፁህነት ማረጋገጫ ንፁህ ሆነው እንዲታዩ ማድረግ። እዚህ ላይ ጋዜጠኛው የማያውቀው ወይም የዘነጋው አንድ ነገር የኢትዮጵያ ህዝብ የኤርትራን ህዝብ እንጂ የሚያምነው በኢሳያስ የሚመራው የኤርትራ መንግስት ሊያጠፋው የቋመጠ መሆኑን ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆኑን ነው፡፡ ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘለዓለም እርስ በርሱ እየተባላ ሲፋጅ እንዲኖር «በመቶ ዓመት የማይፈቱት የቤት ሥራ እሰጣቸዋለሁ» ብሎ መዛቱን አይዘነጋውም፡፡ እናም አምባሳደር ግርማ በቪኦኤ የሰጡትን ማስተባበያ ሲሰማ «አፈ ቅቤ ልበ ጩቤ» እንደሚላቸው እርግጥ ነው።

አሁን የቪኦኤው ጋዜጠኛ የኤርትራ መንግስት የቀረበበትን ውንጀላ ያለምንም ተጨባጭ ማስረጃ እንዲያስተባብሉ የማድረግ አካሄዱ መነሻ ምን ሊሆን ይችላል? የሚለው ላይ እናተኩር፡፡ እንግዲህ የነፃነት ምድር እንደሆነች የሚነገርላት አሜሪካ፣ የቀይ ሽብር ወንጀለኞች፣ ኢትዮጵያን ከሁለት አሥርት አመት በፊት ወደነበረችበት የብሄር ብሄረሰቦች እስር ቤትነት የመመለስ ዓላማ ያላቸው አድኃሪያን፣ ሙሰኞች፣ በተለያየ ምክንያት አሁን ያለው የመንግስት ስርአት ላይ መሰረተ ቢስ ጥላቻ ያደረባቸው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወዘተ…የመሸጉባት አገር መሆኗን እናውቃለን።

አሜሪካ በመኖራቸው ብቻ ሁሉን የሚያውቁ የሚመስላቸው ቂሎች እንዳሉም እኛ አገር ቤት የምንኖር ኢትዮጵያውያን እናውቃለን። ታዲያ እነዚህ ቂሎች እነርሱ የያዙት አቋም ትልቅ፣ እነርሱ የቀባጠሩት ሁሉ ለውጥ ማምጣት የሚችል የሚመስላቸው ግብዞች ናቸው፡፡ እርግጥ የደርግን አፈናና ግድያ ሸሽተው ሄደው እዚያው የለሙ አገራቸውን በምክንያት ላይ ተመስርተው የሚወዱና የሚያግዙ በርካቶች መሆናቸውንም እንረዳለን። እነዚህ ግን ዝምተኞች ስለሆኑ ያሉ አይመስሉም።

ከኤርትራ መንግስት ጋር አብሮ ኢትዮጵያን በሽብር ለማተራመስ ያለመውና ለዚሁ ዓላማ ማስፈፀሚያነት በቅርቡ 500 ሺ ዶላር የተበረከ ተለት በዶክተር ብርሃኑ የሚመራው ግንቦት ሰባትም የተወለደው እዚያው አሜሪካ ነው፡፡ ታዲያ ዶክተር ብርሃኑ ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የመንግስት ለውጥ ለማምጣት ያደራጁት ግንቦት ሰባት የተባለው ቡድን ከኤርትራ መንግስትና ምናልባት በእጅ አዙር ከሌሎችም አሸባሪዎች ዶላር ስለሚዘንብለት በአንፃራዊነት ገንዘብ ጠገብ ሊባል የሚችል የኢትዮጵያ የመንግስት ሥርአት ተቃዋሚ ነው፡፡ በዚህ ሳቢያ በአሜሪካና አውሮፓ የተቃውሞውን ጎራ ሳይበር ሚዲያ፤ ዌብ ሳይት፣ ፓልቶክ… የመሳሰሉትን ሚዲያዎች ተቆጣጥ ሮታል። ከሻዕቢያ በሚያገኘው የገንዘብ ድጋፍ የሚያን ቀሳቅሰው የራዲዮና ቴሌቭዥን ስርጭትም አለው።

መረጃዎች እንደሚያስረዱት ግንቦት ሰባት በሚል የተሰባሰቡ ሰዎች ጥቂት ቢሆኑም፣ ሚዲያውን ተቆጣጥረው ጯሂዎች በመሆናቸው ብዙ ይመስላሉ። አይነኬዎችም ሆነዋል። ከእነርሱ ትዕዛዝ ያፈነገጠ ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ ከፍተኛ የማጥላላት ዘመቻ ስለሚደረግበት አቋመ ቢስ የሆነውን አንዳንድ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ሁሉ አደናግረውታል።

እንግዲህ አብዛኞቹ በተለይ በደርግ ዘመን አገር ቤት ጋዜጠኞች ሆነው የምናውቃቸውና አሁን በአሜሪካ መንግስት የሚተዳደረው የአሜሪካ ድምፅ የአማርኛ ፕሮግራም ውስጥ የሚሰሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችም «በአይነኬው» ግንቦት ሰባት የማጥላላት ዘመቻ ከሚርዱት ውጭ እንዳልሆኑ አካሄዳቸው ያመለክታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከቪኦኤ ጋዜጠኞች መሃከል የተወሰኑቱ የብሄር ብሄረሰቦች እስር ቤት ወደነበረችው የቀደሞዋ አሃዳዊ ኢትዮጵያ እንድንመለስ የሚያልሙ በመሆናቸው የኢፌዴሪ ሥርአት ላይ ጥላቻ ያላቸው መሆኑን የሚያመለክቱ እውነታዎች አሉ፡፡ ይህ አቋም በተለያዩ አጋጣሚዎች በፕሮግራማቸውም ላይ ይንፀባረቃል።

እንግዲህ የኤርትራ መንግስት ሲወገዝ፣ ውግዘቱ ላዩ ላይ ለተለጠፈው ግንቦት ሰባትም ይተርፋል። በቅርቡ የብሄራዊ መረጃ ደህንነትና የፌዴራል ፖሊስ የጋራ ፀረ ሽብር ግብረ ኃይል በተጨባጭ መረጃ ደርሼበታለሁ ያለው ኢትዮጵያውያን ላይ ሊፈፀም የታሰበ የሽብር ጥቃትና በቤንሻንጉል ጉምዝ በተፈፀመ የሽብር ጥቃት ተጠርጥረው የተያዙት ግለሰቦች «ከኤርትራ መንግስት ጋር ግንኙነት አላቸው» መባሉ አገር ቤትም ውጭም ያሉ ቅን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያ ውያን በኤርትራ ላይ እንዲቆጡ ማድረጉ እርግጥ ነው፡፡

ይህ ደግሞ «ከኢሳያሰ አፈወርቂ ጋር ተባብሬ ነፃ አወጣችኋለሁ» እያለ የቂል ወሬ ለሚዘባርቀው «አይነኬው» ግንቦት ሰባትም ይተርፋል፡፡ እናም «አይነኬው» ግንቦት ሰባት «ኤርትራ ከዚህ ፀያፍ ድርጊት ነፃ ነች» እንድትባል ይፈልጋል። የግንቦት ሰባትን ሳይበር ሚዲያዎቸ የማጥላላት ዘመቻ የሚፈሩት በአሜሪካና አውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የኤርትራ መንግስትን ንፅሕና ከመመስከር ወደኋላ አይሉም፡፡ ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ የቪኦኤ የአማርኛ ፕሮግራም ጋዜጠኞችም ከዚህ የፀዱ ናቸው ብሎ ማሰብ ስህተትነቱ ያይላል፤ በተለይ በተለያየ ፕሮግራማቸው ውስጥ የሚንፀባረቀውን ሚዛናዊነት የጎደለውና የግል ስሜት የሚንፀባረ ቅባቸውን ዘገባዎቻቸውን ላስተዋለ። እናም የቪኦኤ ጋዜጠኞች አምባሳደር ግርማ አስመሮምን ጠርተው «ኢትዮጵያ በሽብርተኝነት ወንጅላችኋለች፣ ማስተባበያ ስጡ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ መልዕክት አስተላልፉ» ብለው የወተወቱት በዚህ ምክንያት ሊሆን ይችላል።

ከዚህ በተጨማሪ ግንቦት ሰባት ከሻዕቢያ የተሰጠውን ገንዘብ ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦችንና ድርጅቶችን ለመግዛትም እንደሚጠ ቀምበትም ዶክተር ብርሃኑ ነግረውናል፡፡ በዚህ መሰረት የቪኦኤ ጋዜጠኞችም እንደ ተፅዕኖ ፈጣሪ ተቆጥረው ተገዝተው ይሆናል የሚል ግምት ያላቸውም አሉ፡፡ ያም ሆነ ይህ የኢትዮጵያ ህዝብ የኤርትራን መንግስት ባህሪ ከምንም በላይ ስለሚያውቀው እንኳን አምባሳደር ግርማ አስመሮም ሌላ ገለልተኛ ሰውም «ኤርትራ ለኢትዮጵያ ክፉ አስባ አታው ቅም» የሚል ማስተባበያ ቢያቀርብ አያምንም። እናም በቪኦኤ በኩል ለታወጀው «የኤርትራ መንግስት፣ ህዝባዊ ግንባር፣ … በኢትዮጵያ ላይ የሽብር ድርጊት አስበው አያውቁም» ለሚለው የአምባሳደር ግርማ አስመሮም ማስተባበያ የኢትዮጵያ ህዝብ ምላሽ «አፈ ቅቤ ልበ ጩቤ» የሚል ነው።
ምንጭ: አዲስ ዘመን ጋዜጣ 

1 comment:

Anonymous said...

for the sake of writing such ideas is non sense.

Post a Comment