(Sept 12, 2013, አዲስ አበባ))--ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ አዲሱ አመት የትራንስፎርሜሽኑን እቅድ በህዝቡ ተሳትፎ ወደ ላቀ ደረጃ የሚሸጋገርበት እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአዲሱ ሚሊኒየም 6ኛ ዓመትን በማስመልከት ለኢትዮጵያ ህዝቦች ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች የኢትዮጵያን ህዳሴ ለማረጋገጥ የተጀመሩት የልማትና የዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ስራዎች ከግብ እንዲደርሱ ህዝቡ የጀመረውን ሚና አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
በዚህም ሂደት የኢ.ፌ.ድ.ሪ መንግስት እንደቀድሞው ሁሉ የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የጀመሩትን የኢትዮጵያ ህዳሴ ዳር የማድረስ አላማ ለማሳካት ከመቼውም ጊዜ በላይ በፅናት እንደሚሰራ አመልክተዋል፡፡
በተመሳሳይ የኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ ብሏል፡፡
ምክር ቤቱ በህገ መንግስቱና በህዝቡ የተጣለበትን ለፈጣን እድገት የሚበጁ ህጎችን በማውጣት አስፈላጊ አካላትን በመከታተልና በመቆጣጠር የህዝቦችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በከፍተኛ የሀላፊነት ስሜት ሲንቀሳቀስ የቆዩ ሲሆን በአዲሱ አመትም ይህንን ተልእኮውን የበለጠ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡
ምክር ቤቱ እየተመዘገበ ባለፈው ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት፣ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታና በመልካም አስተዳደር ውስጥ ሁሉም ዜጋ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅበታል ብሏል፡፡
ክልሎችም የእንኩዋን አደረሳችሁ መልክት አስተላልፈዋል፡፡ የአማራና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳደሮች እንዲሁም የኦሮሚያ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ለመላው የኢዮጵያ ህዝብ አዲሱ ዓመት የሰላምና የብልፅግና ይሆን ዘንድ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡
ምንጭ፡ ኢሬቴድ

No comments:
Post a Comment