(Sept 10, 2013, (አዲስ አበባ))--የኢትዮጵያ የሃይማኖት አባቶች በአዲሱ አመት ልማትና እድገት ማስቀጠል የሁሉም ሃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ አስገነዘቡ፡፡ የዘመን መለወጫ በአልን ምክኒያት በማድረግ የሃይማኖት አባቶች ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አዲስ አመት በሀገራችን የሚካሄዱ የልማት ስራዎችን ከዳር ለማድረስ ቃላችንን የምናድስበት አመት ነው፡፡
ዜጎች በመከባበር፣ በመመካከርና በመረዳዳት በልዩነት ውስጥ ያለውን አንድነት በማጠናከር የሀገሪቱን ልማትና እድገት ማስቀጠል ይገባልም ብለዋል የሃይማኖት መሪዎቹ፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቀዳማዊ ፓትሪያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተ/ሃይማኖት አባ ማትያስ በእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸው መጪው 2006 ዓ.ም ዘመነ ማርቆስ ህዝባችን ሁሉ በማሀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኑሮው የበለፀገ፣ በዕውቀትና ማስተዋል የተካነ፣ ጤንነቱና ሰላሙ የተጠበቀ ይሆን ዘንድ በተሰማራበት የስራ መስክ ጠንክሮ በመስራት ሀገሩን እንዲያለማ አስገንዝበዋል፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዘዳንት ሸህ ኺያር መሃመድ አማንም በአዲሱ አመት ሀይማኖት ሳይለየን እንደህዝብና እንዳገር በጋራ ለአገራችን ልማት ማስቀጠል እምንሰራበት አመት ነው በማለት አዲሱ አመት የደስታ የሰላምና የብልፅግና እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳትና የጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዘዳንት ብፁዕ አቡነ ብርሀነ እየሱስ ሱራፌል ዜጎች በሀገራቸው ጠንክረው በመስራትና ሃብት በማፍራት ኑራችን ሊለዌጡ ይገባል በማለት ህብረተሰብ ልጆቹን በማስተማር በህገወጥ መንገድ ከሀገር የሚወጡ ወገኖችን ከሚደርስባቸው አደጋ እንዲታደግ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ዋቅ ስዩም እዶሳም በበኩላቸው ይህን የዘመን መለወጫ በዓል ስናከብር የታመሙትን በመጠየቅ ወላጅ ላጡ ህፃናት እግዚአብሄር ከሰጠን በረከት በማካፈል እንድንከባከባቸውና በአሉን አብረናቸው እንድናከብር አደራ ያሉ ሲሆን እግዚአብሄር አዲሱን 2006 ዓ.ም የሰላም፣ የጤና የልማትና የብልፅግና አመት እንዲያደርግልን ተመኝተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ዋና ፀሀፊ ቄስ ዓለሙ ሼጣም በሀገራችን እየተካሄደ ያለውን የእናቶችና ህፃናትን የጤና እንክብካቤ የተሳካ ይሆንም ዘንድ ሁሉም በጋራ እንዲንቀሳቀስም ነው ያሳሰቡት፡፡
በመጨረሻም ሁሉም ዜጎች ኢትዮጵያዊነት መንፈስ የእድገት ዋስትና የሆነውን ሰላም በንቃት መጠበቅ እንደሚገባው የሁሉም የእምነት ተቋማት አባቶች አስገንዝበዋል፡፡
ምንጭ፡ ኢሬቴድ

No comments:
Post a Comment