(ሰኔ 04/2005, (አዲስ አበባ))--የሻዕቢያ መንግስት ወደ ትግራይ ክልል ሊያስገባው የሞከረው የሽብር ሃይል በህዝብና በፀጥታ ሃይሎች ትብብር ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ
ለኢሬቴድ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው ዘጠኝ አባላት የነበሩት ይህ የሽብር ሃይል ግንቦት 25/2005 ወደ ቃፍታ
ሁመራ በረኸት ቀበሌ ሊገባ ሲሞክር በአካባቢው በነበሩ የፀጥታ ሃይሎችና በህዝቡ በጋራ በተሰነዘረበት ጥቃት ሙሉ
በሙሉ ተደምስሷል፡፡
በጥቃቱ የቡድኑ መሪና ምክትሉን ጨምሮ አምስት አባላቱ ሲሞቱ ቀሪዎቹ አራቱ ደግሞ ተማርከዋል፡፡ ከተገደሉትና ከተማረኩት የሻዕቢያ ተላላኪዎች 3 ኤም ፎርቲን፤ 6 ክላሽንኮቭ፤ 2 የውጊያ መነፅር፤ 15 የእጅ ቦንብ፤ 4 ሞባይል፤ 2490 የተለያዩ ጥይቶችና በርከት ያለ የኢትዮጵያ ገንዘብ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
በህዝባችንና
በፀጥታ ሃይላችን የተወሰደው ርምጃ ለሻዕቢያና ተላላኮዎቹም ሆነ ሌሎች ተመሳሳይ ድርጊት ለመፈፅም የሚሹ ፀረ ሰላም
ሃይሎች ትምህርት ያስተላለፈ ነው ብሏል የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ለኢሬቴድ በላከው መግለጫ፡፡
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ለአካባቢው ህዝብና ለፀጥታ ሃይሎቹ ያለውን አድናቆትም ገልጧል፡፡ በኢትዮጵያ
ላይ ቀጥተኛ ወረራ የማድረግ አቅም እንደሌለው የተረዳው የሻዕቢያ መንግስት በሚያደራጃቸው የሽብር ቡድኖች
አማካኝነት የሃገራችንን ሰላም በማወክ ልማታችንን ለማደናቀፍ የሚያደርገውን ጥረት በንቃት በመከታተል ለማክሸፍ
ያለውን ዝግጁነትም ኮሚሽኑ አረጋግጧል፡፡
ምንጭ፡ ኢሬቴድ
1 comment:
Why is Ethiopia is defending it self instead of teaching this stupid Eritrean blood dictator. Now he is an Arab or an Arab click. Why don't he enjoy his Arabness instead of making trouble with black African Ethiopian?
Please, listen to me, Ethiopian leaders, Isaias will not keep quite unless you send gorilla fighters in to Eritrea. That way he knows, what it means to send Shabya in to Ethiopia.
Post a Comment