(Jun 27, 2013 , (አዲስ አበባ))--ሙስናን ለመከላከል መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ አጠናከሮ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አስታወቁ፡፡ የተለያዩ የንግዱ ማህበረሰብ አካላትን ባሳተፈው የውይይት መድረክ ላይ ሙስና ለንግድ እንቅስቃሴው ከፍተኛ እንቅፋት እየፈጠረ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ተሳታፊዎቹም መንግስት ለችግሩ አፋጣኝ ምላሽ ይስጠን ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም መንግስት የችግሩን አሳሳቢነት ተገንዘቦ እርምጃ እየወሰደ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡
ግባችን አንድ ነው፡፡ ያሉትን እንቅፋቶች በጋራ መጋፈጥ አለብን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ችግሩ ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረትም የንግዱ ማህበረሰብ አባላት የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
መንግስት የግል ባለሀብቶች ሊሳተፉባቸው የሚገቡ ዘርፎችን እያዘጋጀ መሆኑንና በቅርብ ለውይይት እንደሚቀርብ ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ባለስልጣናትን በገንዘብ ለመደለል የሚሞክሩ ባለሀብቶች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠንቅቀዋል፡፡
ምንጭ፡ ኢሬቴድ

No comments:
Post a Comment