Monday, May 13, 2013

የአቶ ገብረዋህድ ባለቤት በቁጥጥር ስር ዋሉ

(May 13, 2013, (አዲስ አበባ))--በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የተያዙት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ ባለቤት ኮሎኔል ሃይማኖት ተስፋይ ባለቤታቸው ከተጠረጠሩት ወንጀል ጋር ተያያዥ የሆኑ ሰነዶችን ሲያሸሹ በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ከፖሊስ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ኮሎኔል ሃይማኖት ከመኖሪያ ቤታቸው ወስደው በሌሎች ግለሰቦች እጅ እንዲደበቁ ያሸሻቸው ሰነዶች በተለያዩ ቦታዎች በአቶ ገብረዋህድ ስም የተመዘገቡ የቤትና የቦታ ካርታዎች ናቸው፡፡
ኮሎኔል ሃይማኖት ካርታዎችን ሲያሸሹ ጥቆማ የደረሳቸው የደህንነትና የፖሊስ ሃይሎችም ክትትል በማድረግ ካርታዎቹን ከተደበቁበት ቦታ ይዘዋቸዋል፡፡
በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ግንቦት 2/ 2005 በቁጥጥር ስር በዋሉት ግለሰቦች ቤት በተደረገው ብርበራ ከፍተኛ መጠን ያለው የኢትዮጵያና የውጭ ሃገራት ገንዘብ እንዲሁም የተለያዩ ሰነዶች መገኘታቸው ይታወሳል፡፡     
ምንጭ፡ ኢሬቴድ
 Home

2 comments:

Anonymous said...

Ethiopians they work so hard to improve their Country but the street smart try to be reach in short cut way there are so much like them .
Keep nail more and more ///

Unknown said...

ወያኔ ራሱ በሙስና የተቋቋመ ድርጅት ነው ወያኔ የተባለ ሁሉ ለፍርድ መቅለብ አለባቸው ስለህ ኢትዮጵያን መምራት ስለማይችሉ ስልጣን ይልቀቁ

Post a Comment