Monday, May 13, 2013

በአንድ ግለሰብ በተከፈተ ተኩስ 12 ሰዎች ተገደሉ

(May 13, 2013, (ባህር ዳር))--በአንድ ግለሰብ በተከፈተ ተኩስ 12 ሰዎች ተገደሉ በባህር ዳር ከተማ ልዩ ስሙ አባይ ማዶ ወይም ቀበሌ 11 በተባለ ቦታ ትናንት ግንቦት 04/2005 ምሽት 2:45 ላይ አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል ባልታወቀ ምክንያት በመነሳሳት ህብረተሰቡ ሰላማዊ እንቅስቃሴውን በሚያደርግበት ወቅት በከፈተው የተኩስ እሩምታ 12 ሰዎችን ገድሏል፡፡


ከሟቾቹ ዉስጥ ህጻናትሴቶችና አዛውንቶች  ይገኙበታል፡፡ በአደጋው የቆሰሉ ሌሎች ሁለት ግለሰቦችም ህክምና እየተደረገላቸው ነው፡፡
ድርጊቱን የፈፀመው ግለሰብ ለማምለጥ ሲሞክር በፀጥታ ሃይሎች ክትትል ሲደረስበት ራሱን ወንዝ ውስጥ መወርወሩን  የአማራ ክልል ፖሊስ አስታውቋል። ፖሊስ በጉዳዩ ላይ እያደረገ ያለውን ምርመራ እንዳጠናቀቀ ተጨማሪ መረጃ እንደሚሰጥ አስታውቋል::
ይህ በእንዲህ  እንዳለ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት ግድያውን አስነዋሪ የጭካኔ ተግባር ሲል አውግዞታል::  ለሟች ቤተሰቦችም መፅናናትን ተመኝቷል:: የሟቾች  የቀብር ስርዓትም በደብረ አባይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን ተፈፅሟል፡፡ 
ምንጭ:  ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት

2 comments:

Anonymous said...

yih bexam asnewar dirgitina chikane yetemolabet sibenabis new. be wogenu lay endih yale dirgit mefetsem aygebam, neger gin gudayun mengist bexibk mayet alebet! yemengist abal honewum yemiyaxeku linoru yichilaluna! le muach beteseboch mestinanatin emegnalehu! manim bihon be gudayu zim malet aygebam!yilma chisha ke mekelle university.

Anonymous said...

Yhe erasenkalemekotater yemeta chekana bendehe ayenetu laye menegesete yemayadagem ermeja beyaweta hulum bemeyezew mesareya bemenorew halafenet yetenekekale beyazute negere ayedelem nedate yemiglstewe.

Post a Comment