Saturday, February 23, 2013

የስድሰተኛው ፓትርያርክ ምርጫ እጩዎች ይፋ ሆኑ

(Feb 23, 2013, አዲስ አበባ)--ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የካቲት 16/2005 ባካሄደው ስብሰባው ለስድስተኛው ፓትርያርክ የሚወዳደሩ ዕጩዎችን ተቀብሎ አጸደቀ። ሲኖዶሱ አስመራጭ ኮሚቴው ባቀረባቸው እጩዎች ላይ ከተወያየ በኋላ ነው ያጸደቀው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትሪያርክ(ኢሬቴድ)
በዚህ መሰረት፦
ብጹእ አቡነ ማትያስ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ፤ብጹእ አቡነ ህዝቅኤል የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሃፊና የከፋ ሸካ ቤንች ማጅ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብጹእ አቡነ ዮሴፍ የባሌ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብጹእ አቡነ ኤልሳእ የሰሜን ጎንደር ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብጹእ አቡነ ማቴዎስ የወላይታ ዳውሮ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በእጩነት ቀርበዋል ብለዋል የአስመራጭ ኮሚቴው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ባያብል ሙላቴ ።
 

የፊታችን ሐሙስ የካቲት 21 አዲስ አበባና ድሬደዋን ጨምሮ ከሁሉም አህጉረ ስብከት የተወከሉ ሊቃነ ጳጳሳት ፤ የአህጉረ ስብከት ስራ አስኪያጆች ፣ ካህናት ፣ ምዕመናንና የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች በእጩዎቹ ላይ ድምጻቸውን ይሰጣሉ። ድምጽ ሰጪዎቹ ቁጥር ስምንት መቶ እንደሆነ ነው አቶ ባያብል የተናገሩት ።
 

በዚሁ ዕለት ምሽት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስድስተኛው ፓትርያርክ ማን ይሆናል የሚለው ምላሽ እንደሚያገኝ ፋና ዘግቧል ። የሚመረጡት ፓትርያርክ እሁድ የካቲት 24/2005 በቅድስት ስላሴ ካቴድራል በሚደረግ ስነ ስርዓት በዓለ ሹመታቸው ይፈጸማል ።
ኢሬቴድ ዜና 

Related topics:
ለስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫ 800 መራጮች ድምፅ ይሰጣሉ 
ቤተ ክርስቲያኗ የስድሰተኛውን ፓትሪያርክ የምርጫ ስሌዳ አወጣች፣ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የጸሎት ሱባዔም ዐወጀች  
የሃይማኖት ተቋማት ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት አገራዊ ንቅናቄ እንፈጥራለን አሉ 
በኢትዮጵያ የሃይማኖት መቻቻልና ተከባብሮ የመኖር እሴት ተጠብቆ እንዲቀጥል ሁሉም ቤተ እምነቶች ጠንካራ ርብርብ ማድረግ አለባቸው    
የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በድምቀት ተከብሮ ዋለ 
የከተራ በዓል በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ተከበረ  

No comments:

Post a Comment