(Wed, 28 March 2012)--ትናንትናና ከትናንት በስቲያ በርካታ ኢትዮጵያዊያን የፌስቡክ ተጠቃሚዎች በእናቷ በከፍተኛ ሁኔታ ስትደበደብ በቪዲዮ የታየችው ሕፃን ማንነት ታወቀ፡፡
ባለፉት ሁለት ቀናት በበርካታ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች የታየው ይህ ቪዲዮ፣ ወ/ሮ ሐሊማት መሐመድ የተባሉት ግለሰብ የሦስት ዓመት ሕፃን ልጃቸውን በአሰቃቂ ሁኔታ ሲደበድቧት ይታያል፡፡ እናትየው ‹‹ያለቀሽበትን ምክንያት ንገሪኝ፣ አንቺን ብሎ ተማሪ፣ ውሸታም፤›› እያሉ በተደጋጋሚ በጥፊ ፊቷን የሚደበድቧት ሲሆን፣ ደረቷንም ሲመቷት ይታያሉ፡፡
ከዚያም ከፊታቸው ከነበረው ጠረጴዛ ላይ ጀላቲ አንስተው ይመጣሉ፡፡ እንደገናም በጀላቲው ይመቷታል፡፡ በዚህን ጊዜም ሜሮን አስናቀ የተባለች በሞባይል ድርጊቱን የምትቀርፀው ወጣት ከትከት ብላ ትስቃለች፡፡
ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባት ሕፃን ግን ድብደባውን የለመደችው በሚመስል ሁኔታ ምንም ዓይነት ለቅሶ በፊቷ ላይ አይታይም፡፡ ሆኖም እናቷ ወ/ሮ ሐሊማት ከፍሪጅ ውስጥ በወጣ በረዶ ደጋግመው ፊቷን ይመቷታል፡፡ ከዚያም በዚያው በረዶ ግንባሯ ላይ ያለውን እብጠት ለማጥፋት ሲያሹላት ቪዲዮ ያሳያል፡፡
ለስድስት ደቂቃ አካባቢ የቆየው ቪዲዮ ለሚመለከተው ሰው ከፍተኛ መሳቀቅን የሚፈጥር ነው፡፡ በፌስቡክ ተጠቃሚዎች መካከል ሲንሸራሸር የቆየውን ይህን ቪዲዮ የአፋላጊ ኩባንያ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ ሪፖርተር ዝግጅት ክፍል ትናንት ጠዋት አምጥተው ሰጥተዋል፡፡ ይህን ድርጊት የፈጸሙትን ግለሰብ ላሳወቃቸው ግለሰብ አሥር ሺሕ ብር እንደሚሰጡ በማስታወቅ በሬዲዮ ማስታወቂያ አስነግረዋል፡፡
ማስታወቂያው በሬዲዮ ሲነገር የቪዲዮው ቀራጭና ቦሌ መድኃኒዓለም አካባቢ በሚገኘው ሴሌክት የምሽት ክበብ ዳንሰኛ የሆነችው ሜሮን አስናቀ ትሰማለች፡፡ ከዚያም ወደ ሸገር ኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ ታዲያስ አዲስ የዝግጅት ክፍል ሄዳ ቪዲዮውን የቀረፀችው እርሷ መሆኗን ትገልጻለች፡፡ ወ/ሮ ሐሊማት መሐመድ፣ ልጃቸውንና ሜሮን አስናቀን መነን አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በሚገኘው ቪዲዮ በተቀረፀበት ቤት አግኝተን አናግረናቸዋል፡፡
እንደ ወ/ሮ ሐሊማት ገለጻ፣ ድርጊቱ የተፈጸመው የዛሬ ሦስት ዓመት አካባቢ መሆኑን ተረድተናል፡፡ በወቅቱ ከባለቤታቸው ተለይተው እርሷን ብቻቸውን እንደሚያሳድጓት የገለጹት ወ/ሮ ሐሊማት፣ ከምትማርበት ትምህርት ቤት በተደጋጋሚ ወላጅ አምጪ በመባሏ የምትባረር ስለመሰላቸውና ቀን ቀን የሚይዝላቸው ባለመኖሩ ምክንያት በንዴት እንደደበደቧት ገልጸዋል፡፡ በጊዜው በከፍተኛ ንዴት ውስጥ ስለነበሩ ሕፃኗን መደብደባቸውን ገልጸዋል፡፡ ‹‹ከሳምንት በኋላ ንዴቴ ሲበርድልኝ ወደ ሐኪም ቤት ወስጄ አሳክሜያት ጤነኛ መሆኗን አረጋግጫላሁ፤›› የሚሉት ወ/ሮ ሐሊማት፣ በወቅቱ ስለተፈጠረው ጉዳይ የኢትዮጵያ ሕዝብንና ቪዲዮውን የተመለከቱ ሰዎችን ጭምር ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡
አሁን የኬጂ 2 ተማሪ የሆነችው ሕፃን በመልካም ጤንነት ላይ የምትገኝ ስትሆን፣ ምንም ዓይነት ሕመም እንደማይሰማትም ለሪፖርተር ገልጻለች፡፡ ስምሽ ማነው ስትባል፣ ‹‹My name is . . . ›› በማለት የምትመልሰው ሕፃን፣ ከዚያ በኋላ ብዙ ተገርፉ እንደማታውቅና ስታጠፋ ብቻ እንደምትቀጣ ገልጻለች፡፡
ቪዲዮውን የምትቀርፀው ወጣት ሜሮን ሕፃኗን ለምን ከድብደባው እንዳላስጣለቻት ስትጠየቅ፣ ‹‹ብዙ ጊዜ በስልኬ ቪዲዮ የመቅረፅ ልምድ አለኝ፡፡ በወቅቱም ቪዲዮውን ቀርጬ ለእናቴ ለማሳየት ፈልጌ ነው፤›› በማለት ምላሽ ሰጥታለች፡፡ በቪዲዮ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የምትስቀው ወጣት ሜሮን፣ ‹‹ደብዳቢዋ ጀላቲ እየመጠጠች ምን ያህል እንደተቃጠልኩ አንቺ አታውቂም?›› በማለቷ ነው የሳቅኩት ብላለች፡፡ ቪዲዮውን ከስልኳ ውስጥ የወሰደችባት የሥራ ባልደረባዋ እንደሆነችም ሜሮን ገልጻለች፡፡
ሕፃኗን ከእናቷ ጋር ባገኘናት ወቅት ተደባዳቢዋ እናት፣ ‹‹በአዲሱ ሚሊኒየም የሕፃናት ደህንነት የሁላችን ኃላፊነት ነው፤ የሚል ቀይ ቲሸርት ለብሰው ነበር፡፡
Source: Reporter

No comments:
Post a Comment