(አዲስ አበባ, መጋቢት 11 ቀን 2004 (አዲስ አበባ) --የኤርትራ መንግሥት የሚያካሂደው የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ ያስፈራቸው የኤርትራ ታዳጊዎችና ወጣቶች አገራቸውን ጥለው መሰደዳቸውን እንደቀጠሉ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር (ዩኤንኤችሲአር) አስታወቀ።
ድርጅቱ ከማይአይኒ የስደተኞች ካምፕ ፅፎት በዓለም ሰብአዊ ጉዳዮች ላይ የሚዘግበውና የሬውተርስ አገልግሎት አካል የሆነው አለርትኔት የተባለው ድረገፅ እንዳሰፈረው ታዳጊዎቹና ወጣቶቹ በኤርትራ ለሻዕቢያ የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ ከመዳረግ ይልቅ ከወላጆቻቸው ጋር በመመካከር ድንበር አሳልፈው ለሚያሻግሯቸው ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለው እየተሰደዱ ነው።
ለደኅንነታቸው ሲባል ዩኤንኤችሲአር ስማቸውን ቀይሮ ከጠቀሳቸው መካከል ገብሬ እንደሚለው የሻዕቢያ የድንበር ጠባቂዎች ካገኙት እሥር ወይም ከዚህ የከፋ ችግር እንደሚጠብቀው እያወቀ ቤተሰቦቹ 25 ሺህ ናቅፋ ወይም 1 ሺህ 650 ዶላር ከፍለው ወደ ሱዳን ተሻግሯል፤ ከዚያም ወደኢትዮጵያ።
የ16 ዓመት ዕድሜ ያለውና ለሻዕቢያ የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ ዕድሜው መድረሱ የተገለፀው ገብሬ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ ከሦስት ዓመት በኋላ በአያቱ ድጋፍ ወደ ካናዳ ለመጓዝ በሂደት ላይ መሆኑን ድርጅቱ አመልክቷል።
በመጠለያ ካምፑ ከሚገኙ ስደተኞች መካከል ከ1 ሺህ 100 በላይ የሚሆኑት ብቻቸውን የተሰደዱ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ታዳጊዎች ድንበር ሲያቋርጡ በሻዕቢያ ወታደሮች ምን ሊደርስባቸው እንደሚችል የማይገነዘቡ ሌሎቹ ደግሞ በአገራቸው ተስፋቸው የተሟጠጠ መሆኑን የድርጅቱ ዘገባ ይጠቁማል፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ቀደም ሲል የተሰደዱ እህት ወይም ወንደሞቻቸውን ለመፈለግ ጭምር ከአገራቸው የኮበለሉ መሆናቸውንም ይገልፃል።
ሌላዋ አበባ የተባለች የ15 ዓመት ልጅ የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጣ የገባችው ከመንደሯ የሦስት ሰዓት ያህል መንገድ ተጉዛ መሆኑን የጠቀሰው ድርጅቱ ወደ ኢትዮጵያ የመጣችውም ግደና የተባለችውን ቀደም ሲል የተሰደደች እህቷን ፍለጋ እንደነበር ጠቁሟል።
እዚህ ስትደርስ ግን እህቷ ወደ እሥራኤል መጓዟንና ከእህቷ ጋር በፈጠረችው ግንኙነት ወደ እሥራኤል በሕገወጥ መንገድ ብትመጣ ወንበዴዎች መንገድ ላይ የአካል ጉዳት ሊያደርሱባትና ልትደፈር እንደምትችል ግደና እንዳስጠነቀቀቻት አስታውቋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ዘ ጋርዲያን የተባለው ታዋቂው የእንግሊዝ ጋዜጣ በድረገፁ የሻዕቢያ መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ ወዳጅ የሌላቸውና ተንጥለው የቀሩ መሪ ናቸው ሲል ገልጿቸዋል።
ኢሳያስ ያቺን አገር በጭካኔና በጡንቻቸው ሥር ማድረጋቸውን፣ ወጣቶቿ እየተሰደዱ መሆናቸውንና እሥርቤቶቿ መሙላታቸውን ሌሎች ምንጮችን በመጥቀስ ጭምር ዘጋርዲያን ዘግቧል።
የሻዕቢያ ወታደራዊና የደኅንነት ባለሥልጣናት በአገሮች ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ሰዎች በሕገወጥ መንገድ ከአገራቸው እንዲወጡ ከማድረግ አልፈው በሕገወጥ የመሣሪያና ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብ ዝውውር ተግባር ውስጥ መዘፈቃቸውንም አስታውቋል።
ባለሥልጣናቱ በዚህ ሕገወጥ ገንዘብና የሻዕቢያ ደጋፊዎች የሚያዋጡትን በመያዝ እንዲሁም አንዳንድ አገሮች የሚሰጧቸውን በመደመር ጭምር በአካባቢው ታጥቀው ሽብር የሚፈፅሙ ኃይላትን እንደሚደግፉ የዘጋርዲያን ድረ ገፅ አስፍሯል።
Source: UNHCR/ENA

No comments:
Post a Comment