(30 December 2011, Reporter)--መስከረም 2 ቀን 2004 ዓ.ም ከምሽቱ 4፡30 ሰዓት አካባቢ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጅ (ሆስተስ) የነበረችውን አበራሽ ኃይላይን፣ በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ ዓይኖቿን በስለት ያጠፋው የቀድሞ ባለቤቷ አቶ ፍስሐ ታደሰ፣ በ14 ዓመታት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ በዛሬው ዕለት ተወሰነበት፡፡
የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ያቀረበውን ክስ ተከትሎ ክሱን ሲመረምር የቆየው የፌዴራል ከፍተኛ ደረጃ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ቅጣቱን የወሰነው፣ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበውን የቅጣት ማክበጃ አስተያየት በከፊል ተቀብሎና ተከሳሹ ያቀረበውን የቅጣት ማቅለያ ሐሳብ ሙሉ በሙሉ በመቀበል ነው፡፡
ጥፋተኛው የተጠቀሰበት የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር አንቀጽ 27(1) እና 539ን ሲሆን፣ አንቀጹ ቅጣትን ለመወሰን ደረጃ ያልወጣለት መሆኑን ገልጾ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ2002 ዓ.ም ያወጣውን የቅጣት አወሳሰን ማንዋል ተከትሎ ውሳኔ መስጠቱን ፍርድ ቤቱ ተናግሯል፡፡
በመሆኑም ደረጃውን ‹‹ከፍተኛ ነው›› በማለት በቅጣት አወሳሰን ማንዋሉ መሠረት እርከን 38 ላይ እንደሚያርፍ አስታውቆ መነሻውን እድሜ ልክ ካለ በኋላ፣ አቃቤ ሕግ ላቀረበው የቅጣት ማክበጃ ሐሳብ አንድ ደረጃ ጨምሮ ወደ እርከን 39 ከፍ ማለቱን ተናግሮ፣ ጥፋተኛው ላቀረበው የቅጣት ማቅለያ ስምንት ደረጃዎችን በመስጠት ወደ እርከን 31 ዝቅ ተብሎ እንዲወሰን መደረጉንም ፍርድ ቤቱ ገልጿል፡፡
በመሆኑም በማንዋሉ መሠረት እርከን 31 የሚያሳየው የቅጣቱ መነሻ 12 ዓመት መሆኑንና ጣሪያው 14 ዓመት ከዘጠኝ ወር መሆኑን ገልጾ፣ ለ14 ዓመታት እንዲታሰርና ከማንኛውም ሕዝባዊ መብቶቹ ለሦስት ዓመት እንዲታገድ ወስኗል፡፡
Source: Reporter
Related topics:
Enough is Enough!

1 comment:
yansewale
Post a Comment