(Sunday, 20 November 2011, Reporter)--የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ‹‹ትግላችን፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ የትግል ታሪክ›› የተሰኘ መጽሐፍ አሳተሙ፡፡ ይህ በሦስት ቅጾች ተከፋፍሎ በተከታታይነት ይወጣል የተባለው መጽሐፍ፣ ቅጽ አንድ ሕትመቱ ተጠናቆ ለገበያ ሊቀርብ መዘጋጀቱ ታውቋል፡፡ የመጀመሪያው ቅጽ 514 ገጾች ሲኖሩት፣ የሽያጭ ዋጋው 39.95 ዶላር ነው፡፡ መጽሐፉ ምስሎችና ካርታዎችን አካቷል፡፡
ኮሎኔል መንግሥቱ በአዲሱ መጽሐፋቸው ማስታወሻ ላይ፣ ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮት ከተቀጣጠለበት እስከተቀለበሰበት ድረስ ያለው ጊዜ ከመሰል ሕዝባዊ አብዮቶች ጋር ስናነፃፅረው በለጋና በአጭር የተቀጨ አብዮት ቢሆንም፣ በአሥራ ሰባት ዓመታት ውስጥ ያደረገውን ፈጣን ጉዞ፣ ያስተናገዳቸውን ሕዝባዊ ተግባሮች፣ የገጠሙትን ፈተናዎችና የጠየቁትን መስዋዕትነት በሦስት ተከታታይ ቅጾች ለማቅረብ ተገድጃለሁ፤›› ብለዋል፡፡
የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆኑ መሪ ግለሰቦች የሚመጡና የሚሄዱ አላፊዎች መሆናቸውን ጠቁመው፣ አገርና ሕዝብ ግን ዘላለማዊ ናቸው፡፡ ይህም ቢሆን በአንድ ታሪካዊ ወቅት መንግሥታት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ያከናወኗቸው ገንቢም ሆኑ አፍራሽ ተግባሮች ማንም ወደደ ጠላ የዚያ አገርና ሕዝብ ታሪክ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
‹‹ትግላችን ስሙ እንደሚያመለክተው በኢትዮጵያ አንድ ትውልድ በሙሉ ቀፎው እንደተነካበት የንብ ሠራዊት ተቆጥቶ በመነሳት ገበሬውን ከገባርነት፣ የሠራተኛውን መደብ ከምንዳ ባርነት፣ ጠቅላላውን ባተሌ ሠርቶ አደር ሕዝብ ከድንቁርና አረንቋና እጅግ አሳፋሪ ከሆነ የዘላለም ድህነት መንጥቆ በማውጣት፣ ራሱንና አገሩን ለመለወጥ በጀመረው ትግል መሪር መስዋዕትነትን ከፍሎ የትግሉን ጣፋጭ ፍሬ ሳይቀምስ፣ አንድነቱንና ሰላሙን ሳያገኝ እንደገና የጨለመበት አሳዛኝ ሕዝብ ልሳን እንጂ፣ አንባቢን በደስታ ለመመሰጥ የተዘጋጀ የሥነ ጽሑፍ ድግስ አይደለም፤›› ሲሉ ኮሎኔል መንግሥቱ ስለ መጽሐፋቸው ይዘት አስገንዝበዋል፡፡
በአብዮት የትግል ጎራ ወይም አሰላለፍ ላይ ብቻ ማተኮራቸውን የገለጹት ኮሎኔል መንግሥቱ፣ ‹‹በብቀላ፣ የአጥቂነት ወይም የተከላካይነት ስሜት አጥቅቶኝ በማጋነን ወይም በማቃለል ታሪኩን ላለማዛባት በተቻለኝ መጠን ከራሴ ጋር ታግያለሁ፤ ከህሊናዬም ጋር ተሟግቻለሁ፤›› ብለዋል፡፡
‹‹ይኼ ትግላችን የተሰኘ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮት ታሪክ ትምርት በመስጠቱ ረገድ ስለሚኖረው ፋይዳ ፍርዱን ለአንባቢው እተዋለሁ፤›› ሲሉ በመጽሐፉ ማስታወሻ ላይ አስፍረዋል፡፡
ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ከመቆጣጠሩ አንድ ሣምንት ቀደም ብሎ ግንቦት 13 ቀን 1983 ዓ.ም. ወደ ዚምባቡዌ መኮብለላቸው ይታወሳል፡፡ ላለፉት 20 ዓመታት እሳቸውን የሚመለከቱ በርካታ መጻሕፍትና መጣጥፎች ለአንባቢያን ቢቀርቡም፣ ይኼኛው መጽሐፋቸው ግን የበኩር ሥራቸው ይሆናል፡፡
ይመሩት የነበረው መንግሥት በፈጸመው የጅምላ ግድያና በሰብዓዊ ፍጡር ላይ በተፈጸመው ወንጀል ከእሳቸውና ከተወሰኑ አመራሮች በስተቀር፣ ከፍተኛ የደርግ ባለሥልጣናት ፍርድ ቤት ቀርበው ክርክር ከተካሄደ በኋላ የሞትና ዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው ነበር፡፡ በቅርቡ ባለሥልጣናቱ በተደረገላቸው ይቅርታ የሞት ፍርዱ ወደ ዕድሜ ልክ እስራት ከተቀየረ በኋላ ብዙዎቹ የእስራቱን ዘመን በመፈጸማቸው መለቀቃቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ኮሎኔል መንግሥቱ ግን በሌሉበት ስለተፈረደባቸውና ይቅርታው ስለማይመለከታቸው አሁንም ተፈላጊ ናቸው፡፡
Source: Reporter

No comments:
Post a Comment