(መስከረም 25 ቀን 2004 , አዲስ አበባ, ኢዜአ)--የናይጀሪያው ፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገቡ።
ፕሬዚዳንት ጆናታን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣በኢትዮጵያ የናይጀሪያ አምባሳደርና ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑ የናይጀሪያ ማህበረሰብ አባላት አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ፕሬዚዳንቱ በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊና ከሌሎች የአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በሁለቱ አገሮች የጋራ፣በአህጉራዊና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
No comments:
Post a Comment