Saturday, October 15, 2011

ቤተክርስቲያኗ የሴት ልጅ ፆታዊ ጥቃትና ግርዛትን የሚያወግዙ መጸሐፍት አሳትማ ለሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር አስረከበች

(ጥቅምት 4 ቀን 2004, አዲስ አበባ)--የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከኖርዌጅያን ቸርች ኤይድ ጋር በመተባባር ያሳተመቻቸውን ሁለት መጸሐፍት ለሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ማስረከቡን የፓትርያርክ ልዩ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።


ልዩ ፅህፈት ቤቱ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ቤተክርስቲያኗ አሳትማ ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር የስረከበቻቸው መጸሐፍት የሴት ልጅ ፆታዊ ጥቃትና ግርዛትን የሚያወግዙ ናቸው።

ቤተ ክርስቲያኗየትዕማር ዘመቻ በፆታዊ ጥቃት ላይእናየሴትልጅ ግርዛት በቤተ ክርስቲያኗ አስተምሮበሚል ርዕስ ያሳተመቻቸው መጸሐፍት በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ ለማስረፅ ያለሙ መሆናቸውንም አመልክቷል። ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በርክክቡ ስነ ሥርዓቱ ላይ እንደገለጸት የሴት ልጅ ጥቃት ማለት የአጠቃላይ ህብረተሰቡ ጥቃት በመሆኑ በሁሉም አካላት ሊወገዝ ይገባል።

የሃይማኖት መሪዎች የሚያገለግሉት ለህዝብ በመሆኑ በበለጠ ማገልገል የሚችሉት ደግሞ ችግሩን ሲያውቁት መሆኑንም ተናግረዋል።

የሴት ልጅ ግርዛት በቤተክርስቲኗ ሃይማኖታዊ ትዕዛዝ አንፃር ሲያይ አግባብነት የሌለው በመሆኑ ፆታዊ ጥቃትና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ማስቀረት የሃይማኖት አባቶች የነቃ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ቅዱስ ፓትርያርኩ አአመልክተዋል።
በዚህ ረገድም የወንዶች አጋርነትና ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፣ ቤተክርስቲያኗ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተባብራ ለመስራት ዝግጁነቷንም አረጋግጠዋል።

የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ፍሬነሽ መኩሪያ በበኩላቸው በአገሪቱ የሚታየው አጠቃላይ ፆታዊ ጥቃት መነሻ ሴቶችን አሳንሶ የሚያይ ህብረተሰብ ስለሚገኝ በመሆኑ ነው ብለዋል።

በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ አብዛኞቹ ጥቃቶች ሃይማኖታዊና ባህላዊ ሽፋን ስላላቸው ከችግሩ ውስብስብነት አንፃር ብዙ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በኩል እየተደረገ ያለው ተሳትፎም ትልቅ ለውጥ ለማምጣት እንደሚረዳም ተናግረዋል።

የኖርዌጂያን ቸርች ኤይድ የኢትዮጵያ ተወካይ ሚስተር ሀንስ በርክላድ በበኩላቸው ሴት ማለት የህብረተሰብ ወሳኝ አካል በመሆኗ ልትከበር ልትጠበቅ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ማንኛውም ዓይነት የሴት ልጅ ጥቃት የሰብዓዊ ጥሰት በመሆኑ በዓለም አቀፍም ሆነ በኢትዮጵያ ህግ ወንጀል ነው ብለዋል።
የኖርዌጂያን ቸርች ኤይድ የሴቶች ጥቃት ለማስቀረት ከኢትዮጵያ መንግሥትና የእምነት ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
ምንጭ: የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት

No comments:

Post a Comment