(መስከረም 8 ቀን 2004 (አዲስ አበባ,ኢዜአ)--ኢትዮጵያ የጀመረችውን የልማት ጥረት ለማሳካት እሥራኤል የምትሰጠውን ሁለንተናዊ የልማት ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለጸች፡፡
በኢትዮጵያ የእሥራኤል ምክትል አምባሳደር አሎን ኡንፋስ አሲፍ ሥርዓተ-ፆታና ልማት ላይ ያተኮረ ዐዉደ ጥናት ዛሬ ሲከፍቱ እንደገለጹት አገሪቱ የኢትዮጵያን የልማት እንቅስቃሴ በማገዝ ድጋፏን አጠናክራ ትቀጥላለች፡፡ እሥራኤል በግብርና፣ በትምህርትና በሥርዓተ-ፆታ ዘርፎች በቅርበት እየሰራች ሲሆን፣ በመስኩ የምታደርገውን እንደምታጠናክር መግለጻቸውን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘገባ ያመለክታል፡፡
በተለይ የኅብረተሰቡ ግማሽ የሚሆኑትን ሴቶች በማብቃት በልማት ያላቸውን ተሳትፎ ማጎልበት እንደሚገባ ምክትል አምባሳደሩ አስገንዝበዋል፡፡ ከዚህ አንጻር የሴቶችን እኩል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሴቶችን አቅም መገንባት ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፣በዚህም ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ድርሻዋን ታደርጋለች ብለዋል፡፡
በእሥራኤል ዓለም አቀፍ የትብብር ማዕከል፣ በግብርና ሚኒስቴርና በጀርመን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር በጋራ የተዘጋጀው ዐውደ ጥናትም ሥርዓተ-ፆታን ከልማት ጋር ማስተሳሰር በሚቻልበት ሁኔታ ግንዛቤ እንደሚያስጨብጥ አመልክተዋል፡፡
የጎልዳ ሜየር ማውንት ካርሜል ዓለም አቀፍ የሥልጠና ማዕከል ባለሙያ ፋኔት ሞዴክ በበኩላቸው ሴቶችን ያላሳተፈ ልማት ምሉዕነት የሚጎድለው በመሆኑ ሥርዓተ-ፆታን በሁሉም ዘርፎች በማካተት ተሳታፊነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ የማዕከሉ የፕሮጀክት አስተባባሪ ሚስስ ሮኒት ጎሎቫትይ አገራቸው የኢትዮጵያን የልማት ጥረት ለመደገፍ የሦስትዮሽ የትብብር ፕሮጄክት ተግባራዊ እያደረገች መሆኗን አስረድተዋል፡፡
የኢትዮጵያና የእሥራኤል ጠቅላይ ሚኒስትሮች እንዲሁም የጀርመን ቻንስለሯ በጋራ በደረሱት ስምምነት መሠረት ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ክልሎች በአነስተኛ የመስኖ ሥራ የሦስት ዓመታት የአቅም ግንባታ ድጋፍ በማድረግ ላይ ናት ብለዋል፡፡
ለአንድ ሳምንት ያህል በሚቆየው ሥርዓተ-ፆታና ልማት ላይ ባተኮረው ዐውደ ጥናት ከአማራ፣ ከኦሮሚያ፣ ከትግራይና ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች የተውጣጡ ባለሙያዎች መሳተፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
No comments:
Post a Comment