(መስከረም 7 ቀን 2004 (አዲስ አበባ, ኢዜአ) --የግብፅና ኢትዮጵያ የሁለትዩሽ ግንኙትን ከጥርጣሬ መንፈስ የፀዳ እንዲሆን ሁለቱ አገሮች በጋራ እንደሚሰሩ ተገለፀ፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በግብፅ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት ካይሮ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደረጎላቸዋል፡፡
አንዱ ግድብ መገደቡ ለሌላኛው ችግር እንደሆነ የሚገልጽ አሉታዊ መልእክት አይኖረንም፣ አንዱ ልማትን ለማምጣት ሲሰራ ሌላው ልማትን ለመገደብ የሚነቀሳቀስ ከሆነ የጋራ ግብ ማስቀመጥ እንደማይቻልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡ ኢትዮጵያ የምትገነባው ግድብ ለሁለቱ አገራት የጋራ ጥቅም የሚውልና ሌሎች የልማት ድልድዩችንም የሚፈጥር ሊሆን እንደሚችልም አቶ መለስ ጠቁመዋል፡፡
የግብፅና የኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ከጥርጣሬ መንፈስ የፀዳ እንዲሆንና ሁለቱን አገራት በኢንቨስትመንትና በንግድ ለማስተሳሳር የሚያስችሉ ስድስት ስምምነቶች መፈረማቸውን የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዘግቧል፡፡
ስምምነቶቹ በግብርና፣ በትምህርት፣ በኢንቨስትመንት፣ በውሃ አቅም ግንባታና፣ ተደራራቢ ቀረጥን በማስቀረት ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን ኢሬቴድ በዘገባው አመልክቷል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ከግብፅ ጠቅላይ ሚኒስር ኤሳም ሸሪፍና የጦር ኃይሎች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሁሴን ታንታዊ ጋር በሁለትዮሽና በእህጉር አቀፍ ጉዳዩች ላይ በተናጠል ውይይት አካሒደዋል፡፡
የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤሳም ሸሪፍ ኢትዮጵያና ግብፅ የጋራ ተጠቃሚ በሚያደርጋቸው ጉዳዩች ላይ ፍጹም የተራራቁ አቋሞችን የሚያራምዱበት ጊዜ ከቀድሞው የግብፅ መንግሥት ጋር እንዳበቃለትም ገልጸዋል፡፡
ሁለቱንም አገራት ተጠቃሚ በሚያደርጉ ጉዳዩች አገራቱ ጠንክረው እንደሚሰሩ ባለስልጣናቱ አመልክተው፣ "በእርግጠኝነት ለነገው ትውልድ በልማት መተባባራችንን እንጂ ችግሮቻችንን ትተንላቸው አናልፍም" ብለዋል፡፡
ሁለቱንም አገራት ተጠቃሚ በሚያደርጉ ጉዳዩች አገራቱ ጠንክረው እንደሚሰሩ ባለስልጣናቱ አመልክተው፣ "በእርግጠኝነት ለነገው ትውልድ በልማት መተባባራችንን እንጂ ችግሮቻችንን ትተንላቸው አናልፍም" ብለዋል፡፡
ባለስልጣናቱ አያይዘውም መንግስታቸው በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ትብር ይበልጥ በማጠናከር በጋራ ጥቅም ላይ ለመስራት ፍላጎት እንዳለውም ገልፀዋል፡፡ በአፍሪካ ችግሮችን ለመፍታት ቀዳሚ የሆኑት ግብፅና ኢትዮጵያ የራሳቸውን ችግር በመተማመን የሚፈቱበት ወቅት ላይ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በበኩላቸው የግብፅና ኢትዮጵያ ግንኙነት ዋነኛ ማእከል በሆኑ ጉዳዩች ላይም ስምምነት መደረሱንና ናይል ድልድይ እንጂ የግንኙት ማነቆ እንዳይሆን መስማማታቸውን ገልጸዋል፡፡
ናይል ለሁሉም በቂ እንደሆነ መስማማታቸውንና አገራቱ አንዱ የሌላውን ጥቅም ሳይነካ ተጠቃሚ ለመሆን እንደሚቻል አስረድተዋል፡፡
አንዱ ግድብ መገደቡ ለሌላኛው ችግር እንደሆነ የሚገልጽ አሉታዊ መልእክት አይኖረንም፣ አንዱ ልማትን ለማምጣት ሲሰራ ሌላው ልማትን ለመገደብ የሚነቀሳቀስ ከሆነ የጋራ ግብ ማስቀመጥ እንደማይቻልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡ ኢትዮጵያ የምትገነባው ግድብ ለሁለቱ አገራት የጋራ ጥቅም የሚውልና ሌሎች የልማት ድልድዩችንም የሚፈጥር ሊሆን እንደሚችልም አቶ መለስ ጠቁመዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ አያይዘውም ግድቡ ኢትዮጵያን፣ ሱዳንና ግብፅን ወደ ተጨማሪ ልማት እንዲመጡ የሚረዳ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡ በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል የጋራ ተጠቃሚኒትን መሰረት ያደረገ አዲስ ግንኙነት መከፈቱን፣ ያለፈው የዜሮ ድምር ጫወታ ማክተሙንና ሁለቱም አገሮች ወደ ኋላ እንደማይመለሱ አቶ መለስ ማረጋገጣቸውን ኢሬቴድን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
No comments:
Post a Comment