Monday, March 13, 2017

በቆሼ በደረሰው አደጋ ህይወታቸው ያለፈ ዜጎች ስርአተ ቀብር ተፈፀመ

(Mar 13, 2017, (EBC))--በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለከተማ ወረዳ አንድ በተለምዶ ቆሼ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በደረሰ የቆሻሻ ክምር መደርመስ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ዜጎች የቀብር ስነ ስርአት ተፈጸመ። በአደጋው ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ዜጎች ቁጥር 65 ደርሷል፡፡ በአደጋው ህይወታቸው ያለፈ ዜጎች በየእምነት ተቋማቶቻቸው የቀብር ስፍራ ነው የቀብር ስነ ስርአታቸው የተከናወነው።የ19 ሰዎች ቀብር በተፈፀመበት የአቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ ድሪባ ኩማ እና የሟቾች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች እና በርካታ ህዝቦች ተገኝተዋል።

የአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ በአደጋው የ45 ሴቶችና የ20 ወንዶች ህይወት ማለፉን ገልጸዋል፡፡ የአካባቢውን ነዋሪዎች የማቋቋም ስራ እና በዘላቂነትም ከተመሳሳይ ችግር ለመታደግ ወደ ሌላ ቦታ እንዲዛወሩ ይደረጋል ብለዋል፡፡ ለዚህም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ድጋፉን እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
ምንጭ: ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን

No comments:

Post a Comment