Wednesday, February 08, 2017

በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ቱርክ ቀዳሚ ሆና እንድትቀጥል የኢትዮጵያ ፍላጎት ነው :- ፕ/ት ሙላቱ ተሾመ

(Feb 08, 2017, (EBC))--የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን ባደረጉላቸዉ ግብዣ ወደ ቱርክ ያቀኑት ፕሬዝዳን ሙላቱ በአንካራ ቤተ መንግስት    ደማቅ  አቀባበል  ተደርጎላቸዋል፡፡ የፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ የቱርክ ጉብኝት በኢትዮጵያ ያፈሰሰችውን የ2 ነጥብ 5 ቢለየን ዶላር መዋዕለ  ንዋይና የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ  ለማጠናከር ነው፡፡



ሁለቱ  መሪዎች በአገራዊ  ሁለትዮሽ ግንኙነታቸው ላይ በዝግ መክረዋል። ከምክክሩ  በኃላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫም ኢትዮጵያ የአፍሪካ የኢንዱስትሪ ማዕከል ለመሆን እየሰራች ነው ያሉት ፕሬዝዳንት ሙላቱ  በዚህም የቱርክ ሚና  ጎልቶ  እንዲወጣ ትሻለች ብለዋል።

"በዉጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ቱርክ አሁንም ቀዳሚ ሆና እንድትቀጥል ኢትዮጵያ ትፈልጋለች፡፡ እኛ በርካታ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለመገንባት ይፋ አድርገናል፡፡ በዚህ ግንባታ ላይ የቱርክ ኩባንያዎችና ባለሃብቶች እንዲሳተፋ ጋብዘናል፡፡ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የቱርክን ባለሃብቶች ለመቀበል ዝግጁ ናት፡፡"

400 የሚሆኑ  ኢትዮጵያዊያ  በቱርክ  ነፃ የትምህርት  ዕድል አግኝታለች ያሉት ፕሬዝዳንት ሙሉት አሁንም ቱርክ መሰል ድጋፏን  እንድታጠናክር ጠይቀዋል። የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን በበኩላቸው የሁለቱ አገራት የንግድ ልውውጥ መጠን  አሁን  ካለብት 439 ሚሊዮን ዶላር፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ አንድ ቢሊዮን ዶላር እንዲደርስ ቱርክ ትሰራለች ብለዋል፡፡ በሃገሪቱ ካሉ የመንግስት ባንኮች ብድር እንዲመቻች በማድረግ የቱርክ ባለሃብቶች እንደግፋለን ያሉት ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ፣ የኢትዮጵያ መንግስትም በተመሳሳይ ለባለሀብቶቹ  ትኩረትእንዲሰጥ ጠይቀዋል። 
ምንጭ: ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን

No comments:

Post a Comment