Wednesday, February 01, 2017

በአገሪቱ ተፈጥሮ በነበረው ሁከትና ግርግር በቁጥጥር ስር የነበሩ 11ሺህ 352 ተጠርጣሪዎች ነገ ይለቀቃሉ

(Feb 01, 2017, (EBC))--በአገሪቱ አንዳንድ አከባቢዎች ተፈጥሮ በነበረው ሁከትና ግርግር በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ 11ሺህ352 ተጠርጣሪዎች ነገ ጥር 25/2009 ዓ.ም እንደሚለቀቁ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ገለጸ። በአገሪቱ የተወሰኑ አከባቢዎች ተፈጥሮ የነበረው ሁከትና ግርግር ተከትሎ በደረሰው ጉዳትና የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው ከነበሩ ዜጎች መካከል 9ሺህ800 ያህሉ በመጀመሪያው ዙር መለቀቃቸው ይታወሳል።የኮማንድ ፖስቱ ሴክሬታሪያትና የመከላከያ ሚንስትሩ አቶ ሲራጅ ፌጌሳ በአገራዊ ሁኔታዎች ላይ የግንዛቤና የተሀድሶ ስልጠና ወስደው ሕብረተሰቡን የተቀላቀሉት እነዚህ ዜጎች ማሕበራዊና አገራዊ ሀላፊነታቸውን መወጣት ጀምረዋል ብለዋል።
ለሁለተኛው ዙር ለሀያ ቀናት የተሀድሶ ስልጠና የወሰዱ 11 ሺህ 352 ተጠርጣሪዎች ደግሞ ነገ እንደሚለቀቁ  አቶ ሲራጅ ተናግረዋል።

ዜጎቹ ሕብረተሰቡን ሲቀላቀሉ አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግላቸውም አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ጥሪ አቅርበዋል።
እንደ ሚንስትሩ ማብራሪያ በቁጥጥር ስር የሚገኙ ቀሪ ተጠርጣሪዎች እንደየፈጸሙት ወንጀል በሕግ የሚጠየቁ ይሆናል።
በአዋጁ የእስከ አሁን አፈጻጸምና ቀጣይ ሂደት ኮማንድ ፖስቱ የሶስት ወር ግምገማ በማድረግ በቅርቡ ለህዝብ መረጃ እንደሚሰጥበትም አቶ ሲራጅ ገልጸዋል።

ምንጭ: ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን

No comments:

Post a Comment