Saturday, May 23, 2015

ሃና ላላንጎን በመድፈር ለሞት የዳረጉ ግለሰቦች ከ17 ዓመት እስከ እድሜ ልክ በሚደርስ እስራት ተቀጡ፡፡

(23 May 2015, አዲስ አበባ ))--የ16 ዓመቷን ታዳጊ ሃና ላላንጎን አስገድዶ በመድፈር ለሞት የዳረጓት አምስት ግለሰቦች ከ17 ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ ቅጣት ተበየነባቸው።



የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ የወንጀል ችሎት ትናንት የሰጠውን ውሳኔ ለጋዜጣው ሪፖርተር የገለጹት፣ ፌዴራል አቃቤ ህግ መኩሪያ አለሙ ተከሳሾች በፈጸሙት ወንጀል የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶባቸው ነበር። ትናንት በዋለው ችሎት የቅጣት ውሳኔ የተሰጠ ሲሆን፤ በዚህ መሰረትም የተከሰሱ አምስት ግለሰቦች ከ17 ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፏል።

አንደኛ ተከሳሽ ሳምሶን ስለሺ እና ሁለተኛ ተከሳሽ በዛብህ ገብረማርያም በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት፤ ሦስተኛ ተከሳሽ በቃሉ ገብረመድህን በ17 ዓመት ጽኑ እስራት፣ አራተኛ ተከሳሽ ኤፍሬም አየለ በ20 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲሁም አምስተኛ ተከሳሽ ተመስገን ፀጋዬን በ18 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጥተዋል።

የፌዴራል ዓቃቤ ህግ አምስቱን ግለሰቦች የአስገድዶ መድፈርና ከባድ የሰው ግድያ ወንጀሎች የሚሉ ሁለት ክሶችን እንደመሰረተባቸው ያስታወሱት ፌዴራል አቃቤ ህግ መኩሪያ፤ ሦስተኛ፣ አራተኛ እና አምስተኛ ተከሳሶች በቀረቡ የተለያዩ ህጋዊ ማቅለያዎች ቅጣቶቹ እንደተቀነሰላቸው ተናግረዋል።
ምንጭ: ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ

Related topics:
የሀና ላላንጎ ጉዳይ በዝግ ችሎት መታየት ጀመረ
ጠጅነሽ የወግነህ ትባላለች ከገበያ ስትመለስ ሶስት ወጣቶች ያደረሱበትን ጥቃት...

No comments:

Post a Comment