Wednesday, September 03, 2014

የግብፅ የውጭጉዳይ ሚኒስትር ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ

(ነሐሴ 28/2006 , (አዲስ አበባ) )--የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ ነገ አዲስ አበባ እንደሚገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምበሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለፁት የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ የአንድ ቀን የስራ ጉብኝት ለማድረግ ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ የፕሬዝደንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ መልዕክት ይዘው እንደሚመጡ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በቆይታቸው በሀለቱ አገራት የጋራ ጉዳዮች ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር  እንደሚመክሩም ይጠበቃል።
ምንጭ: ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
No comments:

Post a Comment